Thursday, March 26, 2015

በኦሮሚያ እና ሌሎች አካባቢዎች የመጠጥ ውሃ ችግር ት/ቤቶችን ከማዘጋት አልፎ ለስደት እየዳረገ ነው

መጋቢት ፲፯(አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በመቶ ሚሊየን በሚገመት ወጪ በታላቅ ፌሽታ እያከበረ የሚገኘው የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር በአንዳንድ የኦሮሚያ አካባቢዎች
ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰውን የመጠጥ ውሃ ችግር ሊታደግ ያልቻለ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ፡፡
ከግብርና ሚኒስቴር የወጣ አዲስ መረጃ እንደሚያሳየው፣ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው የመጠጥ ውሃ ችግር ሕዝብን ለከፍተኛ ችግር ከመዳረጉም አልፎ የመማር ማስተማር ስራ በማደናቀፍ ትምህርት ቤቶችን እስከማዘጋት ደርሷል።
የመጠጥ ውሃ ችግር ከገጠማቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች መካከል በአርሲ ዞን በጎሎልቻ፣ መርቲ፣ .ዝዋይ፣ ዱግዳ፣ ሴሩና ደጁ ወረዳዎች፣ በምዕራብ አርሲ ዞን በሻላ ሲራሮና ሻሸመኔ ወረዳዎች፣ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በሚደጋ፣ ቁምቢያ መዩ ወረዳዎች፣ በምስራቅ
ሸዋ ዞን በቦሰት ወረዳ እና በጉጂ ዞን በሊበንና ሰባቦሩ ወረዳዎች አስከፊ የተባለ የመጠጥ ውሃ ችግር ማጋጠሙን ሚኒስቴሩ አጋልጦአል፡፡
የመጠጥ ውሃ ችግሩ በተለይ በአርሲ ዞን በዝዋይ ዱግዳና በሴሩ ወረዳዎች፣ በጉጂ ዞን በሊበን ወረዳ ት/ቤቶችን እስከማዘጋት የደረሰ ችግር መከሰቱ ተረጋግጦአል፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የተከሰተውን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ ከአጋር ድርጅቶች
ባገኘው ድጋፍ ውሃ በቦቴ የማደል ስራ እያከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡
በቦረና ዞን አንዳንድ ወረዳዎች ማለትም በአሬሮ፣ ድሬ፣ ዲሎ፣ ዳስ የእንስሳት መዳከምና ሞት መከሰት የጀመረ ሲሆን በአርሲና ምዕ/ሐረርጌ ዞኖች የእንስሳቱ አቋም እየተዳከመ መሆኑ፣ የእንስሳት እንቅስቃሴም ተጀምሮ በምዕ/ሐረርጌ ዞን ከቡርቃ ዲምቱና ሃዊ
ጉዲና ወደ ዱንገታና ዋቤ ወንዝ፣ በቦረና ዞን ከተልተሌ ወደ ገራንና ኮንሶ፤ ከድሬ፤ ሚዮና ሞያሌ ወደ ኬንያ (አዋሳኝ ቦታዎች) በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው በሪፖርቱ ተመልክቷል።
የኦሮሚያ ክልል ገዥ ፓርቲ ኦህዴድ/ኢህአዴግ  እንዲህ ዓይነቱን የህዝብ ችግር ሳይፈታ ለክብረበአል በመቶ ሚሊየን ብሮችን ሲያፈስ መታየቱ አሳዛኝ መሆኑን ዘጋቢያችን ያነጋገርናቸው የኦሮሞ ተወላጆች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአማራ ክልል ደግሞ በሰ/ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ፣ በሰ/ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ በእያንዳንዳቸው 3 ቀበሌዎች የውሃ እጥረት፣ በዋግኸምራ ዞን በሳህላ፣ ዝቋላና ሰቆጣ ወረዳዎች፣ በሰ/ወሎ ዞን በላስታና ቡግና ወረዳዎች፣ በደ/ወሎ ዞን በመቅደላ
ወረዳ በ4 ቀበሌዎች፣ በኦሮሚያ ዞን በአ/ፉርሲ ወረዳና በምስ/ጎጃም ዞን ቆላማ አካባቢዎች የውሃ እጥረት ተከስቷል።
በሀረሪ ክልል በ5 ቀበሌዎችና በድሬዳዋ አስተዳደር ቆላማ ቀበሌዎችም ተመሳሳይ ችግር ተከስቷል። ችግሮችን ለመቅረፍ ውሃ በቦቴ ለማደል ሙከራ መደረጉም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

Wednesday, March 25, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልዕክቶች በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን እንዳይተላለፉ እየተደረገ ነው

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መጋቢት 16/2007 ዓ.ም ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ፣ ከተላኩት የቅስቀሳ መልክቶች መካከል ” የመከላከያ ሰራዊቱ ሌሎችም የአገሪቱ ቁልፍ ተቋማት ከገዢው ፓርቲ ካድሬዎች
ውጪ አልሆነም፣ በተለይም በገዛ ሃገራቸው ከስራ ይባረራሉ ፣ ተቋማቱን እውቀት የሌላቸው ካድሬዎች እንዲመሩት ተደርጓል፣ ገዢው ፓርቲ ፖሊስን፣ ሚዲያውን፣ መከላከያ ሰራዊቱን፣ ደህንነቱን ሰማያዊንና ሌሎች ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት ሲጠቀምባቸው ቆይቷል
የሚሉትና ሌሎችም በህገ መንግስቱ የተቋቋሙ የዲሞክራሲ ተቋማትን ህልውና የሚክድና ተግባራቸውን የሚያንቋሽሽ መልእክቶች በመሆናቸውና ህገመንግስቱን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስነምግባር ህጉን እና የድርጅታችንን ኢዲቶሪያል ፖሊሲ የሚጻረሩ ሆነው
ስለተገኙ አይተላለፉም ብሎአል።
ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶቹ እንዳይተላለፉ ሲከለከል የአሁኑ ለ8ኛ ጊዜ ነው፡

ኢህአዴግ የህዝቡ ብሶት አደጋ እንደሚያስከትል አውቋል” ስትል የአዲስ አበባ የኢህአዴግ የሴቶች ሊግ ም/ል ሊቀመንበር ተናገረች

መጋቢት ፲፮(አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሊጉ ም/ል ሊቀመንበር በመሆን ለአመታት ያገለገለችው ወ/ት እየሩሳሌም  አበረ  ከኢሳት ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ “የአዲስ አበባ ህዝብ እንደሚገነፍል ድስት እፍ እፍ እየተባለ  ቢያዝም፣ አሁንም
በርካታ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን እያነሳ ነው” ብላለች።
የታፈነ የመልካም አስተዳደር እና የዲሞክራሲ ጩኸት አለ የምትለው ወ/ት እየሩሳሌም፣ ገዢው ፓርቲም ህዝቡ በከፍተኛ ብሶት ላይ እንደሚገኝና አደጋ ሊያስከትል እንደሚችልም ጠንቅቆ ያውቀዋል ብላለች።
ከምርጫ 97 በሁዋላ ኢህአዴግ የተሳካለት ነገር ቢኖር ተቃዋሚዎችን ማፈን ነው የምትለው ኢየሩሳሌም፣ ህዝቡ በሚታየው ነገር ሁሉ ባለመርካቱ ገዢው ፓርቲ ቁጥጥሩን በማጥበቅ የህዝቡን ብሶት ለማፈን ይሞክራል ስትል አክላለች።
ወ/ት እየሩሳሌም ድርጅቱን ጥላ ስደትን መርጣለች። ለረጅም አመታት የአዲስ አበባ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ እና በሌሎችም የስልጣን ሃላፊነቶች ላይ ሲሰሩ የቆዩት የኦህዴድ ድርጅት አባል የሆኑት ወ/ሮ አበባ ገብረስላሴም በቅርቡ ኢህአዴግን በመተው፣ በአሜሪካ
ጥገኝነት ጠይቀዋል። ከወ/ት እየሩሳሌም ጋር የተደረገው ቃለምልልስ ሰሞኑን ይቀርባል።

Tuesday, March 24, 2015

ኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ግንባታን በየደረጃው የሚቆጣጠረውን ስምምነት ፈረመች

መጋቢት ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በጋራ የፈረሙት አዲሱ ስምምነት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ በሙሉ ነጻነት የምትሰራውን ስራ እንደሚገድብ ከአረብኛ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው  ሰነድ አመልክቷል።
ሰነዱ ኢትዮጵያ ግድቡን ለመገንባት በምታደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴና በየትኛውም የግንባታ ደረጃ ላይ አለማቀፉ አጥኝ ቡድን ለሚሰጠው አስተያየት ተገዢ በመሆን እንድትተገብር ይገልጻል። አጥኝ ኮሚቴው የግድቡ ግንባታ የግብጽንና ሱዳንን የውሃ ድርሻ መጠን
ይቀንሳል ወይም በግብጽና ሱዳን አካባቢያዊ ሁኔታ ላይ ተጽአኖ ያመጣል የሚል ድምደማ ላይ ከደረሰ ካሳ እስከመክፈል የሚያደርስ ግዴታም መጣሉ ተመልክቷል።
አጥኚ ቡድኑ የመጨረሻውን የጥናት ውጤት ይፋ ካደረገ በሁዋላ ሶስቱም አገራት እንደሚቀበሉት የተስማሙ ሲሆን፣ ምናልባት አጥኝ ቡድኑ ግድቡ በግብጽና ሱዳን ላይ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ያስከትላል ብሎ ቢወስን ኢትዮጵያ የግድቡን ቅርጽ እስከመቀየር ልትደርስ ትችላለች።
ኢትዮጵያ የምትገነባው ግድብ፣ ከግብጽና ሱዳን የውሃ ማጠራቀሚያዎችን የሚጎዳ ከሆነም ኢትዮጵያ አገራቱን ፈጥና የማሳወቅና ለውጥ ማድረግ እንደሚኖርባትም ስምምነቱ ይገልጻል።
የስምምነቱ አብዛኛው ክፍል ኢትዮጵያ ስለምትፈጽማቸው ግዴታዎች ትኩረት ያደረገ ነው። ግብጽና ሱዳን ለአባይ ወንዝ የሚያበረክቱት የውሃ ድርሻ ካለመኖሩ አንጻር ስምምነቱ በዋነኝነት ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ ያላትን መብት የሚገድብ ብቻ ሳይሆን፣ የአባይ ግድብ
ግንባታ እጣ ፋንታን ከኢትዮጵያ እጅ አውጥቶ በአለማቀፍ አጥኚዎች እጅ እንዲሆን የሚያደርገው ነው በሚል ትችት እየቀረበበት ነው።
ይሁን እንጅ ሶስቱም አገራት ስምምነቱን በማወደስ ለተግባራዊነቱ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

Tuesday, March 17, 2015

የውሃና ችግር የኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት መነጋገሪያ ሆኗል

መጋቢት (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የሚደርሱት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከትግራይ እስደ ደቡብ ክልል የውሃ ጀሪካኖችን በምንጮችና በውሃ መስጪያ ባንቧዎች ተሰልፈው ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል። በዋና ከተማዋ አዲስ አበባም እንዲሁ በተለያዩ ቦታዎች የውሃ እጥረት ማጋጠሙን የየክልሉ ሪፖርተሮች ከሚልኩት እለታዊ መረጃ ለመረዳት ይቻላል።

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት  በአሜሪካ የደረሰባቸው ተቃውሞ በጠ/ሚ ሃይለማርያም፣ ጌታቸውን አሰፋ፣ ኢሳትና ሌሎች ሃይሎች የተቀነባበረ ነው አሉ

መጋቢት (ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በአንድ ኢትዮጵያዊ ከፍተኛ ተቃውሞ ያገጠማቸው አቶ አብዲ ሙሃመድ ተቃውሞውን ያቀነባበሩት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ፣ ኢሳት ፣ ግንቦት7 እና የኤራትራ መንግስት በጋራ በመሆን ነው ሲሉ አካራ ኒውስ በተባለው የግል ዌብሳይታቸው ላይ በሶማልኛ ባወጡት ረጅም ጽሁፍ ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ ተቃውሞውን ሲያሰማ የነበረውን መኮንን የተባለውን ሰው ስም ከፊት በማስቀደም፣ መኮንን ጌታቸው አሰፋ ሃይለማርያም ብለው ጽሁፋቸውን ይጀምሩና  ኢሳት ከጀርባ ሆኖ ሲያቀናብር እንደነበር ያትታሉ።
የተቃውሞው እቅድ መክሸፉን የሚገልጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ኢሳት ቴሌቪዥንም ፕሬዚዳንቱ ሲናገሩት የነበረውን ንግግር ጥሩ ቢሆንም ሆን ብሎ እንዳይተላለፍ ያደረገው፣ እቅዱ መክሸፉን በመረዳቱ ነው ብለዋል።
በወጣው ጽሁፍ ዙሪያ አስተያየቱን የጠየቅነው በአንድ ወቅት የፕሬዚዳንት አብዲ የግል አማካሪ፣ የሶማሊ ክልል ወጣቶች ፕሬዚዳንትና የዚህ ዌብሳይት መስራች የሆነው፣ በአሁኑ ጊዜ በስዊድ አገር በስደት ላይ የሚገኘው ሰብአዊ መብት ተማጓቹ ወጣት አብዱላሂ ሁሴን ፣ አካራ ኒውስ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2009 በፕሬዚዳንቱ ትእዛዝ መከፈቱንና እርሱ የውብሳይቱ ሃላፊና መስራች ሆኖ መስራቱን  ገልጿል። ዌብሳይቱ ለልዩ ሚሊሺያ ከተመደበው የመንግስት በጀት ተቀንሶ መቋቋሙን የሚገልጸው አብዱላሂ፣ በዌብሳይቱ ላይ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች ገንዘብ የሚከፈለውም ከክልሉ ባጀት መሆኑን ይናገራል።
አብዱላሂ ዌብሳይቱን ሲመራ በነበረበት ወቅት ያገኛቸውን ቁልፍ የቪዲዮ ማስረጃዎች በመያዝ ከአገር ከወጣ በሁዋላ፣ ዌብሳይቱ በፕሬዚዳንቱ ታናሽ ወንድም በከድር ሙሃመድ ኡመር ስም እንዲመዘገብ መደረጉን አስረድቷል። በውብሳይቱ ላይ የሚወጣውን ማንኛውንም ጽሁፍ በቃል እየተናገረ የሚያስጽፈው ፕሬዚዳንቱ መሆኑን አብዱላሂ ገልጿል።
አቶ አብዲ፣ የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋና ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተቃውሞውን አቀነባብረውታል ብሎ እንደሚያምን የገለጸው አብዱላሂ ምክንያቱ ደግሞ ከወራት በፊት ከተፈጠረው ክፍፍል ጋር ይያያዛል ብሎአል። የክልሉ የምክር ቤት አባላት 7 ለ5 በመወሰን አቶ አብዲን ከስልጣን ለማውረድ ሙከራ ቢያደርጉም፣ አቶ አብዲ ሀረር በሚገኙት በወዳጃቸው በጄኔራል አብራሃ አማካኝነት በስልጣን ላይ እንዲቆዩ መደረጉን አስታውሷል።
7ቱ የምክር ቤት አባላት አሁንም ተሰደው አዲስ አበባ እንደሚገኙ የሚገልጸው አብዱላሂ፣ በአቶ ሃይለማርያምና በአቶ ጌታቸው አሰፋ እንደሚደገፉም ገልጿል። አቶ አብዲ ለአቶ ሃይለማርያም ከፍተኛ ንቀት ያላቸው ሲሆን፣ ከእርሳቸው የሚመጣውን ትእዛዝ አይቀበሉም። አቶ አብዲ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ሰላም እንደሆኑ ለማሳየት ሁለቱ ሰዎች ጎን ለጎን ቁጭ ብለው የሚያሳይ ፎርጅድ ፎቶግራፍ አሰርተው በዚሁ ዌብሳይት ላይ እንዲወጣ ካደረጉ በሁዋላ፣ በደረሰባቸው ነቀፋ እንዲነሳ አድርገዋል።
በአቶ አብዲ ጉዳይ በአንድ በኩል የደህንነት ሹሙና አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የመከላከያው ሹም ጄኔራል አብርሃ ተፋጠው እንደሚገኙ የሚገልጸው አብዱላሂ፣ እስካሁን ባለው ሂደት መከላከያ በማሸነፉ እነ አቶ ሃይለማርያም ምንም ለማድረግ ሳይችሉ ቀርተዋል ብሎአል።
ፕሬዚዳንቱ ወደ አገር ሲመለሱ ችግር አይገጥማቸውም ወይ ተብሎ ለተጠየቀው ሲመልስ ደግሞ፣ የመከላከያ ባለስልጣናት እጃው ውስጥ እስካሉ ድረስ ምንም እንደማይሆኑ ይናገራል። ነገሮች ገፍተው ከመጡም ውብሳይቱ የእኔ አይደለም ሊሉ እንደሚችል አክሏል።
በመከላከያ አዛዦችና በአቶ አብዲ መካከል ያለው ግንኙነት ከግል ጥቅም ጋር የተሳሳረ መሆኑንም አብዱላሂ ይናገራል ። አቶ አብዲ ከኦብነግ ጋር የሚደረገው ድርድር ስልጣኔን አደጋ ውስጥ ይጥለዋል በሚል ስጋት አይቀበሉትም።
የአካራ ኒውስ ውብሳይት መተዳዳደሪያ ጽሁፍ እንደሚያሳየው ፣ ዌብሳይቱ ስለሶማሊ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ከባለስልጣኖች አንደበት የሚነገረውን እየተቀበለ እንደሚያሰራጭ ያትታል። በዌብሳይቱ ውስጥ የክልሉ ፕሬዚዳንት የሚያደርጉዋቸው እንቅስቃሴዎችና የአሜሪካ ጉብኝታቸው በፎቶ ተደግፎ ቀርቧል።
በተመሳሳይ ዜና ደግሞ አቶ አብዲ በሚኒሶታ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞቻዋል። በተቃውሞው ላይ  የሶማሊ ተወላጆች ኢትዮጵአውያንና ሌሎች ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመሆን አቶ አብዱላሂ እናቶችን የሚገድል፣ ጨፍጫፊ፣ ገዳይ የሚሉ የተቃውሞ ድምጾችን አሰምተዋል
የሶማሊክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሃመድ ኡመር እና በክልሉ የካቢኔ አባሎች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ተከትሎ በጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጽ/ቤት በተካሄደው አስቸኳይ ግምገማ ፣ ፕሬዚዳንቱ ፈጸሟቸው የተባሉ በርካታ ወንጀሎች ተዘርዝረው ቀርበዋል።
ባለፈው ነሃሴ ወር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በሰብሳቢነት በመሩት ግምገማ ላይ ም/ል ጠ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የጠ/ሚኒስትሩ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ አለቃ ጸጋየ በርሄ፣የደህንነትምክትልሹሙኢሳያስ ወጊዮርጊስ፣የምስራቅእዝዋናአዛዥጄኔራልአብርሃበቅጽልስማቸውኳታር፣የፌደራልፖሊስወንጀልመከላከልሃላፊ ጄ/ልግርማየመንጁስ፣አቶአዲሱለገሰ፣አቶአብዲመሃመድናየተለያዩየክልሉየካቢኔአባላትእንዲሁምሌሎች 2 የኢህአዴግከፍተኛአመራሮችም በተገኙበት
አቶ አብዲ መገምገማቸውን ኢሳት ዘግቦ ነበር።
አቶአብዲስልጣንከያዙጀምሮእሳቸውበሚመሩትሚሊሺያበብዙመቶዎችየሚቆጠሩሰዎችበተለያዩምክንያቶችመገደላቸውን፣በርካታ ሲቪሎችታስረውህክምናሳይገኙበቀላፎ፣በፌርፌርናበሌሎችምእስርቤቶችእንዲሞቱ
ማደረጋቸቸውን፣ ከመንግስት የተመደበውን ግዙፍ በጀት ለአንዳንድ የፌደራል ባለስልጣናት በተለይም ለጄ/ልአብርሃ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በተለያዩ ወቅቶች እንዲሰጣቸው በማድረግና በተለያዩመንገዶች ከፍተኛ
ገንዘብእንዲዘርፍማድረጋቸው፣ የአገርሽማግሌዎችንበመሰብሰብ በአንቀጽ 39 መሰረትየራሳችንንመንግስት ስለምናውጅለዚህታሪካዊክስተትራሳችሁንአዘጋጁ፣ፌደራልመንግስትምበውስጥጉዳያችንጣልቃመግባትአይችልምብለውመናገራቸው፣
የልዩ ፖሊስ አባላትና የጎሳ አባላሎቻቸው ከፍተኛ ገንዘብ እንዲዘርፉ ማሰማራታቸው ፣በክልሉ የሚካሄዱትንትላልቅፕሮጀክቶችያለጫራታበመስጠትሆንብለውለብዝበዛአዘጋጅተዋልየሚሉ የግምገማ ነጥቦች ቀርበውባቸው ነበር።
በግምገማውወቅትጄ ልአብርሃበአቶአብዲላይየቀረበውንግምገማአጥብቀውመቃወማቸው ለአቶ አብዲ የስልጣን እድሜ መራዘም አስተዋጽኦ ማድረጉ በወቅቱ ተዘግቧል።

Monday, March 16, 2015

የኦሞ ስኳር ፕሮጀክቶች ግጭቶችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አለማቀፉ ቡድን አስጠነቀቀ

የተለያዩ የአለም አገራትን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክንና ለጋሽ ተቋማትን ጨምሮ27 አባላትን የያዘውዲቨሎፕመንት አሲስታንስ ግሩፕ የተባለ አለማቀፍ ቡድን፤ በደቡብ ኦሞ በመከናወን ላይየሚገኙ ሰፋፊ የመንግስት የስኳር ፕሮጀክቶች በአካባቢውግጭቶችን ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ ባለፈው ረቡዕማስጠንቀቁን ብሉምበርግ ዘገበ፡፡
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር / ሽፈራው ተክለ ማርያም በበኩላቸው፤ በደቡብ ኦሞ የሚከናወኑ የልማትስራዎች ግጭትን ለመከላከል ያለሙእንደሆኑና በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦችም የልማት ዕቅዶቹንበተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል በስፋት መሰራቱን ከብሉምበርግጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅተናግረዋል፡፡ 
የስኳር ኮርፖሬሽን ከቻይና ልማት ባንክ ባገኘው ብድር በደቡብ ኦሞ አካባቢ ስድስት የስኳር ፋብሪካዎችንለመገንባትና 150 ሺህ ሄክታር ላይየሸንኮራ አገዳ ልማት ለማከናወን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የጠቆመውዘገባው፣ የሸንኮራ አገዳ ልማቱ የአካባቢውን ነባር ነዋሪዎች አኗኗርሊያቃውስ ይችላል ተብሎ እንደሚሰጋ ቡድኑማስታወቁን ገልጧል፡፡

Sunday, March 15, 2015


አደባባይ በመውጣት ሀሳባቸውን በመግለጽ ተለይተው የሚታወቁት ዳኛቸው በዩኒቨርስቲው ለሰባት ዓመታት አስተምረዋል፡፡ ዶክተሩ በአደባባይ በሚያደርጓቸው ተሳትፎዎች ደስተኛ ያልነበሩት ህወሓቶች ለዳኛቸው በሚቀርቧቸው ሰዎች አማካኝነት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ካልሆነም አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ሲወተውቷቸው ቆይተዋል፡፡
ከወራት በፊት በዩኒቨርስቲው የሚያቆያቸውን ኮንትራት ለመፈረም ሲንቀሳቀሱ ዶክመንታቸው ከዩኒቨርስቲው መዝገብ ክፍል ተፈልጎ መጥፋቱ ሰዎቹ ሊያባረሯቸው እንደወሰኑ ፍንጭ እንደሰጣቸው በወቅቱ መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
በዩኒቨርስቲው ለሰባት ዓመታት ላስተማሩ መመህራን የሚሰጠው የእረፍት ጊዜ ተፈቅዶላቸው እረፍት ለመውጣት ሲጠባበቁ በብጣቂ ወረቀት መሰናበታቸው እንደተነገራቸው የሚገልጹት ዳኛቸው ‹‹አሁን ገና ኢትዮጵያዊ መሆኔን አወቅኩ ምክንያቱም መበቴ ተረገጠ››በለዋል፡፡
ዶክተር መረራ ጉዲና ትናንት ምሽት በተላለፈው የምርጫ ክርክር ወቅት‹‹ኢህአዴግ ምሁራንን አይወድም››በማለት መናገራቸውን የሚያስታውሱ የዳኛቸው ስንብት መንስኤ ምን እንደሆነ በደንብ ይገነዘቡታል፡፡
Like ·  · 

Friday, March 13, 2015

አርሶ አደሮች ገንዘባችንን ተቀማን አሉ

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በብአዴን አመራሮች እና በግንባር ቀደም አርሶ አደሮቸ ላለፉት አምስት አመታት የወረቀት ፈብሪካ ለመገንባት በሚል ከተሸላሚ አርሶ አደሮች የተሰበሰበው በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገማ እንደማይታወቅ አርሶ አደሮች ተናግረዋል። ገንዘባቸው እንዲመለስልቸው ቢወተውቱም  ምላሽ ማጣታቸውን ተናግረዋል።
በሰባተኛው የአርሶአደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች ስብሰባ ላይ የተገኘው ዘጋቢያችን   ያነጋገራቸው አርሶ አዶሮች “ከአምስት አመታት በፊት በሁለተኛው እና በሶስተኛው የአርሶ አደሮች በዓል ላይ በክልሉ ካቢኔ ጎትጓችነት የኢንዱስትሪ አክሲዩን ባለቤት ትሆናላችሁ በሚል ጥሪታችንን አሟጠን፣  ከ70ሺ ብር ጀምሮ በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ብናዋጣም እስካሁን ምንም ነገር ለማየት አልቻልም” ብለዋል።
ከስራ አሰፈፃሚው አቶ አለምነው መኮንን በተገኝ መረጃ መሰረት የአማራ ፐልፕ የወረቀት ፋብሪካን ለመገነባት ሙሉ በሙሉ ከተሸላሚ አርሶ አደሮቸ አክሲዩን እንዲዋጣ ተደርጎ  ከ 21 ሚልዩን ብር በላይ ተሰብስቧል። 

መንግስት በውጭ የሚኖረውን ዲያስፖራ ለመያዝ ይረዳኛል በሚል ከጀመራቸው የቤት ልማት ፕሮግራም ውስጥ 40 በ60 በሚባለው ፕሮግራም የሚገነቡ ቤቶች ከምርጫ 2007 በፊት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ሳይችል ቀረ፡፡

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሚቀጥለው ሳምንት ከመጋቢት 10 እስከ 13 ድረስ ባሉት ቀናት የአዲስአበባ አስተዳደር 20 በ80 ተብሎ
የሚታወቀውን የኮንዶሚኒየም 35 ሺ ቤቶች ዕጣ በማውጣት ለእድለኞች ለማስተላለፍ ያቀደ ሲሆን በዚህ የዕጣ አወጣጥ ፕሮግራም ላይ 40 በ 60 የሚባለውና አብዛኛው ዲያስፖራ ተመዝግቦበታል የተባለው ዕጣ እንደማይወጣ ታውቆአል፡፡
የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ሰሞኑን በተካሄደው የአስተዳደሩ ም/ቤት ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንደጠቆሙት 1 ሺ 200 ያህል 40 በ 60 የተገነቡ ቤቶች ግንባታቸው ባለመጠናቀቁ በመጪው ሰኔ ወር ለማስተላለፍ ዕቅድ ተይዞአል፡፡
ለዚህ ለ40 በ 60ፕሮግራም  የተመዘገበው 164 ሺ 779 ሕዝብ ሲሆን ለአንድ መኝታ ቤት በየወሩ 1 ሺ 33 ብር፣
ለሁለት መኝታ ቤት በየወሩ 1 ሺ 575 ብር፣ ለሶስት መኝታ ቤት በየወሩ 2 ሺ 453 ብር እየቆጠበ ይገኛል፡፡ ይህ የቤት ልማት ፕሮግራም ከሌላው ለየት የሚያደርገው መንግስት ምንም ዓይነት ድጎማ የማያደርግበትና ዕድለኞች የቤቱን ሙሉ ወጪ ከፍለው እንዲወስዱ የታሰበ መሆኑ ነው፡፡
በዚሁ መሰረት 40 በመቶ ባለዕድለኛው ሲከፍል 60 በመቶውን ከባንክ በሚገኝ ብድር ባለቤት ለማድረግ ታስቦ የተጀመረ ቢሆንም፣ በኃላ ላይ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ መቶ በመቶ ቅድሚያ ለከፈለ ቅድሚያ ያገኛል የሚል በአንድ ወቅት መግለጫ መስጠታቸው ብዙዎችንተስፋ አስቆርጦአል፡፡
የአስተዳደሩ ምንጮች እንደሚናገሩት ይህም ሆኖ በርካታ ሰዎች መቶ በመቶ በመክፈላቸውና ቁጥራቸውም ከሚገነቡት ቤቶች በላይ በመሆኑ በዕጣ መለየት የግድ ሆኖአል፡፡
ምንጮቹ አያይዘውም የአስተዳደሩ ጥቂት ሃላፊዎች 40 በ60 ቤቶች መቶ በመቶ ቅድሚያ ለከፈሉ ቅድሚያ ይሰጥ የሚለው ከፕሮግራሙ ዓላማና ለሕዝብ ከተገባው ቃል ተቃራኒ በመሆኑ መተግበር የለበትም የሚል አቋም እንዳላቸው ታውቋል፡፡
በመሃል ከተማ በሰንጋ ተራና ክራውን ሆቴል አካባቢ  ጂ 12 እና ጂ 9 በሚል  የተገነቡት እነዚሁ ቤቶች ከተመዝጋቢው ቁጥር አንጻር ሲታይ  እጅግ አነስተኛና እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን የጠቀሱት የአስተዳደሩ ምንጮች፣  የዘንድሮውን አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በዓመት 1 ሺ 200 ቤቶች ይገነባሉ ቢባልም፣  164ሺ ቤት ለመገንባት ስንት ኣመት ሊፈጅ እንደሚችል ሲታሰብ ሥራው በመንግስት አቅም ብቻ ሊከናወን እንደማይችል በቂ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ ሳምንት  እጣ ከሚወጣባቸው ቤቶች ውስጥ  1 ሺህ ቤቶች የ10 በ90 ማለትም ስቱዲዮ ክፍል ያላቸው ሲሆኑ፥ 34 ሺዎቹ ደግሞ የ20 በ 80 ወይንም ኮንዶሚኒየም የሚባሉት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ናቸው።
የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በየካ አባዶ፣ ቦሌ ለሚ፣ ቦሌ ቡልቡላ እና ቱሉ ዲምቱ ሳይቶች እንደሚገኙ ታውቆአል፡፡

የግዲቾ ብሄረሰብ አባላት ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊሶች አንድ ሰው ገድለው 8 አቆሰሉ

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግዲቾ ብሄረሰብ አባላት ተቃውሞውን ያስነሱት መሬታቸው ለትምባሆ ተክል እርሻ ለአንድ ባለሀብት መሰጠቱን ተከትሎ ነው።
በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በምእራብ አባያ ወረዳ የሚኖሩት ቁጥራቸው እስከ 5 ሺ የሚደርሱ የብሄረሰቡ አባላት፣ ቀደም ብሎ በአባያ ሃይቅ መካከል በሚገኘው ደሴት ይኖሩ ነበር። ደሴቱ በሃይቁ ሙሉ በሙሉ መሸፈኑን ተከትሎ የብሄረሰቡ አባላት ሃንቲ ወደ ሚባል አጎራባች ቀበሌ በመሄድ ኑሮአቸውን ሲገፉ ቆይተዋል።
ይሁን  እንጅ የዞኑ ምክር ቤት የእርሻ መሬታቸውን ለ4 ኢንቨስተሮች በመስጠቱ፣ ነዋሪዎቹ በእርሻ መሬት እጦት ሲሰቃዩ ቆይተዋል። ባለፉት ጥቂት ወራት ደግሞ የብሄረሰቡን አባላት ሙሉ በሙሉ በሚያፈናቅልና መድረሻ በሚያሳጣ ሁኔታ ፣ መሬታቸው ለአንድ ትምባሆ አምራች ኢንቨስተር ተሰጥቷል።
ነዋሪዎቹ  በተወካይ ሽማግሌዎች አማካኝነት አቤቱታቸውን ለዞኑና ለክልል ምክር ቤት አባላት ሲያቀርቡ ቢቆዩም፣ በየደረጃው ካሉ ባለስልጣናት ያገኙት መልስ ግን ስድብ ብቻ ነው።
ባለፈው ማክሰኞ አዲሱ ባለሃብት ወደ አካባቢው በመሄድ ደኖችን  መመንጠር ሲጀምር በአካባቢው የነበሩት ሴቶችና ህጻናት በመጮህ ተቃውመዋል። የአካባቢው ፖሊሶች ፈጥነው በመድረስ በጩኸት ሲቃወሙ ከነበሩት መካከል አንዷን አሮጊት ክፉኛ መደብደባቸውን፣ ጨኸቱን ሰምተው የተሰባሰቡት ወንዶችም ተቃውሞአቸውን መግለጻቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
ፖሊሶች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ያገኙትን ሁሉ ከመደብደብ አልፈው ጥይቶችን በመተኮስ አንዱን የብሄረሰቡ አባል በ4 ጥይቶች አናቱን መትተው ሲበታትኑት፣ 8ቱን ደግሞ ክፉኛ አቁሰለዋቸዋል። አንደኛው ሰው አንጀቱ አካባቢ ተመትቶ የህክምና እርዳታ እያገኘ ቢሆንም፣ ላይተርፍ ይችላል ተብሎአል። ሌሎች ደግሞ እጅና እግራቸው መሰባበሩን የአይን እማኖች ለኢሳት ተናግረዋል።  
“በጣም የሚያሳዝነው” ይላሉ ነዋሪዎች፣ “ሟቹ ለ6 ሰአታት ያክል መንገድ ላይ ወድቆ አስከሬኑ እንዳይነሳ መደረጉ ነው”።
የብሄረሰቡ አባላት በከፍተኛ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ መሬታቸው በጉልበት ለባላሀብቱ ከተሰጠ፣ ወደ ከተሞች ተሰደው የጎዳና ተዳዳሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይናገራሉ።
በጉዳዩ ዙሪያ የጋሞጎፋ ዞን ፖሊስ ጽ/ቤትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።

Thursday, March 12, 2015

በሲዳማ ዞን የአለታ ጩኮ ወረዳ ህዝብ በውሃ እና መብራት ማጣት እየተሰቃየ ነው

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳው ውሃ ከ15 ቀን በላይ በመጥፋቱ ከጉረቤት ቀበሌያት እየተቀዳ የሚመጣው ንፅህናው ያልተጠበቀ አንድ ጀሪካን ውሃ እስከ 10 ብር እየተሸጠ ሲሆን ፣  ይህንኑ ውሃ በአህያ ጋሪ ከተማ ውስጥ ለመግዛት ነዋሪዎች ቀድመው ለመክፈል ይገደዳሉ ።
አንዲት የጪኮ01 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችና በሰው ቤት የቀን ስራ ሰርታ የምትተዳደር ሴት  ” እቤቴ የአንድ አመት ልጅ አለኝ ልጄ በውሃ ጥም እየሞተ ነው ይኸው አንድ የታሸገ ውሃ በእጅዋ ይዛ እያሳየች ይህንን ለልጄ ስል በ15 ብር ገዛሁ ግን አቅሜ እንኳን ለታሸገ ውሃ ለዳቦም አልበቃ” ብላለች ።
ሌላውም አርሶ አደር ልጆቼን ከትምህርት ቤት አስቀርቻለሁ ምክንያቱም ውሃ በሌለበት አምኜ ከተማ ልጆቼን አልክም ብለዋል ። በአንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች ቤት ውሃ ለሊት ለሊት የሚመጣ ሲሆን ስለዚሁ ጉዳይ የተጠየቁት የውሃ ጵ/ቤት ሃላፊ አቶ መኩሪያ፣ ችግሩ የተከሰተው ዋናው የውሃ ታንከር የሚያንቀሳቅሰው የኤሌክትሪክ መስመር በመበላሸቱ ምንም ማድረግ አልችልም በማለት ድፍን ያለ ምላሽ ሰጥተዋል ።
የወረዳው አስተዳደር ጉዳዮን ለመፍታት ያደረገው ሙከራ የለም የሚሉት ነዋሪዎች ለራሱ ቢሮ ጄኔሬተር በመግዛት እና የታሸገ ውሃ ለሃላፊዎች በማቅረብ የህዝቡን ችግር ረስቶታል ሲሉ መናገራቸውን የአካበባው ወኪላችን ገልጿል

አቶ በረከት ስምኦን ራሳቸውን ከምርጫ ክርክር አገለሉ

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአለማቀፍ ታዛቢዎችና በኢትዮጵያውያን በቂ ትኩረት ያልተሰጠውን የግንቦት 16 ቀን 2007 ምርጫ ክርክር የሚሳተፉለትን መሪዎች ሲያፈላል የነበረው ኢህአዴግ፣ ለመጀመሪያው ዙር የክርክር መድረክ የሚሆኑትን ሰዎች ሲመርጥ፣ አቶ በረከት ራሳቸውን አግልለዋል።
ኢህአዴግ 23 አመራሮችን ለክርክር በእቅድ የያዘ ቢሆንም፣ ከእነዚህ ወስጥ በመጀመሪያው ዙር መጣሪያውን ያለፉት አቶ  ሬዲዋን ሁሴን  እና አቶ ደሰታ አስፋው ብቻ ናቸው። 21ዱ አመራሮች ቀጥተኛ ተፎካካሪ መሆን አይችሉም ተብለዋል።
በሁለተኛው ዙር ማጣራት አቶ አባይ ፅሃየ ፣ካሳ ተክለብርሃን ፤ ተፈራ ደርበው ፤ሽመልስ ከማል እንዲያልፉ ተደርጓል። ኢህአዴግ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማህደር ሲያጠና ከርሞ ዛሬ በዝግ ለተከራካሪ አመራሮች ገለጻ እያደረገ ነው።
በመጀመሪያው ዙር በእጩነት ቀርበው አይመጥኑም፣ ኢህአዴግን ያዋርዱታል ከተባሉት ውስጥ አባ ዱላ ገመዳ፣ አስቴር ማሞ፣ ዘነቡ ታደሰ፣ ሙፈሪያት ከማል፣ ከበደ ጫኔ፣ ወልዱ ይምሰል፣አህመድ አብተው፣ ተመስገን ጥላሁን፣ አሊ ሲራጅ፣ ታደሰ ሃይሌ፣ ፍሬህይወት አያሌውና ብስራት ጋሻው ይገኙበታል።
በረከት ስምኦን በክርክር መድረኮች ላይ እንዲገኙ ቢጠየቁም አልፈልግም በሚል ራሳቸውን አግልለዋል። ራሳቸውን ለማግለላቸው የሰጡት ምክንያት የለም።  ከመጋቢት 04 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በሚካሄደው የፓርቲዎች ክርክር ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግን ጨምሮ በአንድ የክርክር መድረክ ላይ አምስት ፓርቲዎች የሚሳተፉ  ሲሆን በአጠቃላይ ዘጠኝ መድረኮች ይካሄዳሉ።
ፓርቲዎቹ በተመረጡት አጀንዳዎች ላይ ያላቸውን አቋም በሚገባ ለማንጸባረቅ በአንድ የክርክር መድረክ የሚሳተፉት ፓርቲዎች ብዛት አምስት እንዲሆን ተደርጓል። በክርክሩ ላይ ተቃዋሚዎች እያንዳንዳቸው አንድ ተከራካሪ  እና  አንድ አማካሪ እንዲሁም ገዢው ኢህአዴግ ሁለት ተከራካሪና አንድ አማካሪ  በመያዝ ይከራከራሉ። የዘንድሮውን ምርጫ የአውሮፓ ህብረት አይታዘበውም። ህብረቱ በምርጫው መሳተፍ ዋጋ የለውም በሚል ምክንያት መሆኑን በቅርቡ በህብረቱ ውስጥ በተዘጋጀ አንድ ዝግጅት ላይ ተገልጿል።

እንግሊዝ ከሰብአዊ መብቶች ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ማቋረጡዋን አስታወቀች

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉምበርግ የእንግሊዝ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው እንግሊዝ በኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለመደጎም ትሰጥ የነበረውን እርዳታ ያቋረጠችው፣ መንግስት መጪውን ምርጫ ተከትሎ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን ማሰሩንና መዋካቡን በመቀጠሉ ነው።
የእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ተራድኦ ጸሃፊ ጀስቲን ግሪኒንግ ፣ እንግሊዝ አጠቃላይ የሆነ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑዋን ተከትሎ፣ ቀድም ብሎ ይሰጥ የነበረው የማህበራዊ አግልግሎት ድጋፍ እንደተቋረጠ ለእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው አስረድተዋል።
ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ የሚፈጸመው የሰብአዊ ና የፖለቲካ ነጻነቶች ገፈፋ አሳሳቢ መሆኑ እርዳታው እንዲቋረጥ አድርጎታል። በተለይም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ ነጻ ምርጫ የማካሄድና የጸጥታ ሃይሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ለተወሰደው እርምጃ ምክንያት መሆኑን ባለስልጣኑ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።
የእንግሊዝ ተራድኦ ድርጅት በዚህ አመት 368 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም በኢትዮጵያ ብር 11 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመስጠት አቅዳ ነበር፧ ባለፉት አምስት አመታት ከ700 ሚሊዮን ፓውንድ ያላነሰ ገንዘብ ደግፋለች

እንግሊዝ ከሰብአዊ መብቶች ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ማቋረጡዋን አስታወቀች

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉምበርግ የእንግሊዝ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው እንግሊዝ በኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለመደጎም ትሰጥ የነበረውን እርዳታ ያቋረጠችው፣ መንግስት መጪውን ምርጫ ተከትሎ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን ማሰሩንና መዋካቡን በመቀጠሉ ነው።
የእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ተራድኦ ጸሃፊ ጀስቲን ግሪኒንግ ፣ እንግሊዝ አጠቃላይ የሆነ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑዋን ተከትሎ፣ ቀድም ብሎ ይሰጥ የነበረው የማህበራዊ አግልግሎት ድጋፍ እንደተቋረጠ ለእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው አስረድተዋል።
ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ የሚፈጸመው የሰብአዊ ና የፖለቲካ ነጻነቶች ገፈፋ አሳሳቢ መሆኑ እርዳታው እንዲቋረጥ አድርጎታል። በተለይም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ ነጻ ምርጫ የማካሄድና የጸጥታ ሃይሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ለተወሰደው እርምጃ ምክንያት መሆኑን ባለስልጣኑ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።
የእንግሊዝ ተራድኦ ድርጅት በዚህ አመት 368 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም በኢትዮጵያ ብር 11 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመስጠት አቅዳ ነበር፧ ባለፉት አምስት አመታት ከ700 ሚሊዮን ፓውንድ ያላነሰ ገንዘብ ደግፋለች

የአዲስ አበባ ከንቲባ የከተማዋን የጸጥታ ጉዳይ ለኦሮምያ ምክር ቤትም ሪፖርት እንዲያቀርቡ ታዘዙ

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባንና የኦሮምያን የጸጥታ ሁኔታ ለማስተሳሰር፣ የኦሮምያን ልዩ ሃይልና የፌደራል ፖሊሶችን በጋራ በአዲስ አበባ ለመጠቀም ሲባል፣ መስተዳድሩ የጸጥታ ጉዳዮችን ለጨፌ ኦሮምያም ጭምር ሪፖርት እንዲያደርግ ታዟል።
የእቅዱ ዋና ነዳፊ የሆኑት የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አባይ ጸሃየ፣ ጸጥታን በተመለከተ የኦሮምያ ምክር ቤት ሪፖርት እንዲቀርብለት፣ የልማት ጉዳዮችን በተለይ መሬትን በተመለከተ ደግሞ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሪፖርት እንዲቀርብለት አዘዋል። ምርጫው ተጠናቆ አዲስ ምክር ቤት እስከሚመሰረት ድረስ በዚህ መንገድ እንዲቀጥል  አባይ ጸሃየ ቢያዝዙም፣ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ሳይቀበሉት ቀርተዋል። ትእዛዙ ወደ ምክትል ከንቲባው አባተ ስጦታው እንዲወርድ ቢደረገም፣ አቶ አባተ ኦሮምኛ አይችሉም በሚል አቶ ድሪባ በግድ እንዲቀበሉት ተደርጓል።
ከንቲባ ድሪባ ጨፌ ኦሮምያ ተገኝተው ሪፖርት የቃረቡ ቢሆንም፣ ከምክር ቤት አባላት የተነሱትን ጥያቄዎች መመለስ ሳይችሉ ቀርተዋል። ከንቲባ ድሪባ ” የአዲስ አበባ የጸጥታ ጉዳይ ለምርጫው ሲባል በኦሮምያ ምክር ቤት እንዲደመጥ ተወስኗል” ብለዋል።
በአዲሱ አሰራር የኦሮምያ ክልል ምን እንደሚያገኙ የጠየቁት የምክር ቤት አባላት በቂ ምላሽ አላገኙም። ይሁን እንጅ አሁንም መሬት ለማስፋት፣ የኦሮምያና የአዲስ አበባ ክልሎችን በማጣረስና ውሳኔዎችን በመደራራብ ችግር ለመፍጠር ታስቦ የተካሄ እንዳይሆን ፣ አካሄዱም ኢህአዴግን ለከፋ ችግር ሊዳርገው እንደሚችል ተናግረዋል።

Wednesday, March 11, 2015

የኢትዮጰያ መንግስት  በተያዘው ዓመት 3 ሚሊዮን ለሚጠጉ ሰዎች እርዳታ  እንደሚያስፈልገው ማሳወቁን ተመድ ገለጸ።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተመድ የመንግስትን ሪፖርት ዋቢ አድርጎ ባወጣው መግለጫ ዘንድሮ  በኢትዮጰያ 2.9 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል።
ከተረጅዎቹ መካከል 38 በመቶው  ከኦሮሚያ፣ 31 ከመቶው ደግሞ ከሶማሌ፣ 12 በመቶው ከትግራይ እና 6 በመቶው ካማራ ክልሎች መሆናቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል። ለተረጅዎቹ ድጋፍ ለማድረግ  386 ሚሊዮን ዶላር  እንደሚያስፈልግ ያመለከተው ተመድ፤ ይሁንና  የረድኤት ድርጅቶች የፈንድ እጥረት እንዳለባቸው በመግለጽ ላይ መሆናቸውን ጠቁሟል።
በተያያዘ ዜና የጋምቤላ ክልል ባለስልጣናት  ከጋምቤላ ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ  በሚገኝ ቦታ <<ጄዊ>> የተሰኘ  አዲስ ካምፕ ማዘጋጀታቸውን የጠቀሰው ተመድ፤ 50 ሺህ ሰዎችን የመያዝ አቅም ይኖረዋል የተባለው ይህ ካምፕ  ስደተኞች ወደ ማምረት ስራ እንዲገቡ የሚያመች እንደሆነ  ቅኝት ለማድረግ ወደ ስፍራው ተንቀሳቅሰው የነበሩ የስደተኞች ጉዳይ  ከፍተኛ ኮሚሺነር ቡድን  አባላትን በመጥቀስ ገልጿል።
አዲሱን ካምፕ ለማሳደግና ለማስፋፋት የኮሚሺኑ ተጨማሪ 16.5 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው በሪፖርቱ ተመልክቷል። ተመድ የመንግስትን ሪፖርት ተንተርሶ  ዘንድሮ  በኢትዮጰያ 2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሰዎች   አስቸኴይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ያወጣውን ሪፖርት  እንደማይቀበሉት ኢሳት ያነጋገራቸው  አንድ የረድኤት ድርጅት ሰራተኛ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ መንደር  ነዋሪዎች በውሀ፣ በመብራትና በስልክ ችግር ክፉኛ እያማረሩ ነው።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነዋሪዎቹ  ምሬታቸውን ለኢሳት ሲግልጹ፦” አቶ ሀይለማርያምን  ከልባችን አውጥተን ከጣልነው ቆይተናል” ብለዋል።
በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን   የጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ የትውልድ ቦታ የሆነችው  የአረካ ከተማ ነዋሪዎች እንዳሉት  በጠቅላላ የወላይታ ዞን  ነዋሪዎች በውሀ፣በመብራትና በስልክ ችግር  መማረር ከጀመሩ ረዥም ጊዜያት ሆኗቸዋል።
በተለይ ካለፉት ሁለት ወራት  ወዲህ የአቶ ሀይለማርያም የትውልድ መንደር በሆነችው  በአረካ አገልግሎቱ ጠቅላላ የቆመበት ደረጃ ላይ መድረሱን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ በዚህም ሳቢያ  አንድ ጀሪካን ውሀ እስከ 15 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን  ጠቁመዋል።
የወረዳው ብቻ ሳይሆን  በአጠቃላይ የዞኑ ህዝብ  ጠቅላይ ሚኒስትሩን  እየረገመና እያወገዘ እንደሚገኝ የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ “እንዲህ የቀለዱብን ብንመርጣቸውም፣ባንመርጣቸውም ኮሮጆ የመገልበጥ  ልምዱን ስለተካኑበት ነው” ብለዋል።
“ህዝቡ እጅግ ተማርሯል፤ ወደ ጨለማ ዘመን እየተመለስን ነው፣ ምን እናድርግ? ብሶታችንን ለማን እንናገር?” ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ተስፋ አድርገን የነበረ ቢሆንም፤ ገዥው ፓርቲ በሆነ ባልሆነው ሰበብ እየፈለገ እያጠፋቸው ነው።”ብለዋል።
ችግሮቹን አስመልክተው ለሚመለከታቸው አካላት በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢያቀርቡም ምንም ዓይነት ተግባራዊ ምላሽ ሊያገኙ አለመቻላቸውን የተናገሩት  የአርኪያ ነዋሪዎች፤ “ወዴት እንሂድ?”ሲሉ  ምሬታቸውን ገልጸዋል

በኢትዮጰያ ህዝባዊ ስብሰባዎችና ሰልፎች  ቢታገዱም ህዝቡ በስርዓቱ ላይ ያለውን ተቃውሞ በተለያዩ መንገዶች መግለጹን ቀጥሏል።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በተለይ በአዲስ አበባ በተለያዩ ስፍራዎች  የሚገኙ ግድግዳዎችና የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች በየእለቱ “ጭቆና በቃን! ነጸነትና ፍትህ እንፈልጋለን!  ለነጸነት ትግል ተነስ!” በሚሉ መፈክሮች አሸብርቀው መታየታቸው የተለመደ ሆኗል።
በቅርቡ ደግሞ  እነኚሁ  የፍትህና  የነጻነት ጥያቄዎች በመገበያያ የብር ኖቶች ላይ ሳይቀር በስፋት  እየተስተዋሉ መሆናቸው  የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሂደቱ በዚህ ከቀጠሉ  የብር ኖቶች በሙሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በመፈክር ጽሁፎች መጥለቅለቃቸው እንደማይቀርም መረጃውን ያደረሱን አካላት  ገልጸዋል።
ከዚህም ባሻገር የአንዳንድ ነጋዴዎች ምርቶች ሳይቀር በታሰሩ የነጻነት ታጋዮች ስም ተሰይመው መታየታቸውን የግለጹት ምንጮች፤ይሁንና  ይህ የሆነው በስም መገጣጠም ይሁን አለያም አምራቾቹ ሆነ ብለው በነጻነት ታጋዮቹ ስም ሰይመው በእርግጥኝነት እንዳላወቁ አልሸሸጉም።
ከነዚህ ምርቶች መካከል በየሱቆች በስፋት እየተሰራጬ የሚገኘው “ርእዮት ሳሙና” አንዱ ነው።
ጉዳዩን አስመልክቶ  የ ርእዮት እህት እስከዳር ዓለሙ በፌስ ቡክ ገጿ ባሰፈረችው አስተያየት ፦”የእኛሰፈርሱቆችይህንንምርትበየመደርደሪያቸዉሞልተዉትሳይይህችልጅበጽሑፏለማፅዳትየሞከረችውአልበቃብሏትበፈሳሽሳሙናመልክመጣችእንዴ?ብዬአሰብኩ ” ብላለች።
ባለፉት ወራት በቦሌ አካባቢ የሚገኙ ግድግዳዎችና አጥሮች ፦”መሪዎቻችን  ይፈቱ!  ፍትህ ለኮሚቴዎቻቸን! ጭቆናው ይብቃ!”በሚሉና በሌሎች መሰል መፈክሮች  ተሞልተው መታየታቸው ይታወሳል።

የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት በዋሽንግተን ዲሲ  ለደረሰባቸው የኢትዮጰያውያን ተቃውሞ የብልግና ምላሽ ሰጡ።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሱማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በዋሽንግተን ዲሲ ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጠማቸው።
ፕሬዚዳንቱ በተገኙበት ሆቴል የተገኙ ኢትዮጰያውያን ፦” ሰውዬው እጃቸው በደም የተጨማለቀ፣ የሱማሌ ክልል ወጣቶችን በመግደል በዘር ማጥፋት ክስ የተመሰረተባቸውና  እና ለዚህም  በዓለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ሊጠየቁ የሚገባ  ወንጀለኛ መሆናቸውን በማውሳት ከፍ ያለ ተቃውሞ አሰምተዋል።
በደረሰባቸው ድንገተኛ ተቃውሞ  የተበሳጩ የመሰሉት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ  በተደጋጋሚ ጸያፍ ቃል ሲናገሩ ተደምጠዋል። ስለ ሁኔታው መረጃ ደርሰሠቸው በስፍራው የደረሱ የሴኩሪቲ ሰራተኞችም   ተቃውሞውን አብረደውታል።

Tuesday, March 10, 2015

ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በአየር ሃይል አባላት ላይ እየዛቱ መሆናቸው ተሰማ

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አብራሪዎች ባለፉት 6 ወራት ከድሬዳዋ አየር ሃይል ግቢ ጠፍተው ተቃዋሚዎችን መቀላቀላቸውንና መሰደዳቸውን ተከትሎ ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑስ በቀሪዎቹ ላይ የዛቻና የማስፈራሪያ ንግግሮችን በማድረግ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል ።
የአየር ሃይል ምንጮች እንደተናገሩት፦ጀነራሉ <<ከጠፉት የአየር ሃይል አባላት ጋር ግንኙነት ነበራቸው>>ያሏቸውንና  <<ሊጠፉ ሲሉ ተያዙ የተባሉ ሌሎች የአየር ሃይል አባላትን>>  ለቀሪዎቹ አባላት ሲያሳዩ ሰንብተዋል። ኢታማዦር ሹሙ  ሰሞኑንም እነኚህኑ <<ከተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት አላቸው>> ያሏቸውን አባላት፦ ” የውስጥ ተቃዋሚዎች” ተያዙ በማለት በተለያዩ የአየር ሃይል ግቢዎች እያዞሩ በማሳየት ሌሎችን የአየር ሀይሉን አባላት ለማስፈራራት ሙከራ በማድረግ ላይ መጠመዳቸው ታውቋል።
እንደ ምንጮች ገለጻ፦ <<ሊጠፉ ሲሉ ተያዙ>> የተባሉ የተለያዩ የአየር ሃይል አባላት  የእስረኛ ህጋዊ መብታቸው ተገፎ በሌሎች የአየር ሃይል አባላት ፊት ቀርበው እንዲሸማቀቁና ክብራቸው እንዲነካ መደረጉ፤ ብዙ የአየር ሃይል አባላትን አስቆጥቷል።
እነዚሁ የአየር ሀይል ምንጮች፤አብራሪዎቹ እውነት ተቃዋሚዎች ናቸው ቢባል እንኳ ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ታስረው ሰራዊቱ ፊት እንዲቀርቡ መደረጉ የአገዛዙን ባህሪ ያሳየነ ነው በማለት  ለኢሳት ገልጸዋል።
የአየር ሃይል አባላት አምነውበት ማገልገል ሲገባቸው በማስፈራራት በሰራዊቱ ውስጥ እንዲቆዩ ለማድረግ የሚደረገው መኩራ ቁጣንና ቅሬታን ከማባባስ ውጭ የሚፈይደው ነገር እንደሌለም እነዚሁ  የአየር ሀይል አባላት ተናግረዋል።
ጄ/ል ሳሞራ  ከዚያም አልፈው ፦<<ኢሳት ኤርትራ ውስጥ ቃለ-መጠይቅ ያደረገላቸውን አብራሪዎችንና ቴክኒሻኖችን ይዘን እናመጣቸዋለን>> እያሉ ሲዝቱ እንደነበር፤ በግምገማ ተወጥረው የሰነበቱት የአየር ሃይል አባላት ተናግረዋል።
በአየር ሃይል አባላትና- በሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦች መካከል መተማመን መጥፋቱን የሚናገሩት እነኚሁ የአየር ሀይል ባልደረቦች፣ በዚህም ምክንያት ጄ/ል ሳሞራና ሌሎች አዛዦች ግራ እንደተጋቡ አክለዋል።
በመጀመሪያ <<ምን እናድርግላችሁ?>> በሚል የማባበል ቃል  መቀራረብ ለመፍጠር ቢሞክሩም  ሰራዊቱ የሚያነሳው የመብት ጥያቄ በቀላሉ የሚመለስ ሆኖ ባለመገኘቱ ወደ ማስፈራራት መገባቱን የአየር ሃይል አባላቱ ይናገራሉ።

2 ዳንኤል ሺበሺ
3 የሽዋስ ዛሬ በዋለው ችሎት የፍርድ በቱን ችሎት በመድፈር ምክንያት ተብሎ የ7 ወር የእስር ፍርድ የተፈረደባቸው ሲሆን አብርሃ ደስታ ወደ ማዕከላዊ እንዲመለስም ታዞዋል።
በተያያዘ ዜና እነ ሃብታሙ አያለው ደግሞ ለመጋቢት 3 ተቀጥረዋል።
Unlike ·  · 

Monday, March 9, 2015

በጋምቤላ የድንበር ከተሞች ዜጎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እየተገደሉ ነው

የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆኑ የጋምቤላ አካባቢዎች ኢትዮጵያውያን በየጊዜው እንደሚገደሉና የጸጥታው ሁኔታ እየተበላሸ መሆኑን በተለያዩ የመንግስትና የግል ስራዎች ላይ የተሰማሩ ዜጎች ገልጸዋል።
መታሃር፣ ላሬ፣ ኢታንግ እንዲሁም ፑጊዶ በሚባሉ አካባቢዎች ማንነታቸው በውል የማይታወቁ ታጣቂዎች አብዛኛውን ጊዜ በግል ኩባንያዎች ተቀጥረው በሚሰሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው። እነዚህ ታጣቂ ሃይሎች የሚወስዱትን እርምጃ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስና ልዩ ሃይል አባላትም በንጹሃን ዜጎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወስዱ ነዋሪዎች ይገልጻሉ። የካቲት 13 ቀን ማቲያስ ዘነበ የተባለው የታያም ኢንጂነሪንግ ኩባንያ አማካሪ ተገድሎ አስከሬኑ ወደ ደብረዘይት ተሸኝቷል። በሌሎች አካባቢዎችም እንዲሁ በየጊዜው ሰራተኞች እየተገደሉ አስከሬናቸው ወደ መሃል አገር እንደሚሸኝ ይናገራሉ።
በአካባቢው የሚታየውን የመሬት መቀራመት በመቃወም የአካባቢው ተወላጆች በተቀጣሪ ሰራተኞች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ አድርጓቸዋል የሚሉት ነዋሪዎች፣ መንግስት በቂ የሆነ እልባት ማስገኘት እንዳልቻለም ያክላሉ።
በእርሻ ስራ ላይ የተሰማሩ አንዳንድ ውስጥ አዋቂዎች እንደሚናገሩት በጋምቤላ ከውጭ አገር ባለሃብቶች ቀጥሎ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን የያዙት የህወሃት ባለስልጣናት ናቸው። በተለይ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ባለቤት ወ/ሮ አዜብ መስፍንና የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ አባይ ጸሃየ ዘመዶች እጅግ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን እንደያዙ ጉዳዩን የሚያውቁ ሰዎች ይናገራሉ። ወ/ሮ አዜብ በተር ፍላይ አግሮ እንዱስትሪ (butterfly Agro Industry) በተበለ ኩባንያቸው ሰፊ መሬት ይዘው ቢቀመጡም፣ ቦታውን እስካሁን አላለሙትም። እንደነዚህ ሰዎች አገላለጽ፣ የባለስልጣኖቹ ዘመዶች ሰፋፊ ቦታዎችን ከክልሉ ባለስልጣናት ይረከቡና ከባንክ ብድር ይወስዱበታል፣ በተበደሩት ብድር ግን የእርሻ ቦታውን ከማልማት ይልቅ፣  ሌሎች ስራዎችን ይሰሩበታል።
የጋምቤላ መሬት ከህወሃት ባለስልጣናት በተጨማሪ፣ ቀድሞ የህወሃት የጦር መኮንኖች በነበሩ ሰዎች ቁጥጥር ስር እንደሚገኝም ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ።
የህገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ ስደተኞች አርብ እለት ወደ ሰሜን ሱዳን ሲጓዙ በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ። የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሱዳን ትሪቢዩን የዓይን ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፤ ከህገ ወጥ አሻጋሪዎቹ መክከል ሁለቱ ህይወታቸው ማለፉ ተመልክቷል። እንደ ሱዳን ፖሊስ ገለጻ አደጋው የደረሰው ከካርቱም 79 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘውና አል-ባካ ተብላ በምትጠራው አካባቢ ባለው “የሺሪያን አል-ሺማጅ” የቀለበት መንገድ ላይ ነው። እስካሁን ከተጎጆዎቹ መካከል 15ቱ መሞታቸው ታውቋል። አሽከርካሪዎች ብዙውን ጊዜ ከተፈቀደው ፍጥነት በላይ የሚያሽከረክሩበት ይህ የቀለበት መንገድ ፤ ቀደም ሲልም ተደጋጋሚ አደጋውችን እንዳስተናገደ የፖሊስ ሪፖርት ያመለክታል። በመሆኑም ከተገቢው ፍጥነት በላይ የሚያሽከረክሩትን ከመቅጣት በተጓዳኝ በቀለበት መንገዱ ላይ ፍጥነት የሚያነብ ኤሌክትሮኒክ ቦርድ ለመስቀል ንቅስቃሴ መጀመሩን የሱዳን ፖሊስ አስታውቋል። ዓለማቀፉ የሰብ አዊ መብት ተሟጋች- ሂዩማን ራይትስ ዎች የሱዳንን እና የግብጽ ፖሊሶችን በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ይከሳቸዋል። የዓይን ምስክሮች ለሱዳን ትሪቢዩን እንደተናገሩትም የሁለቱ ሀገራት ፖሊሶች ህገ-ወጥ አሻጋሪዎቹን ሲይዙ ከማሰር ይልቅ ከነሱ ጋር በመተባበር ሁኔታዎችን እንደሚያመቻቹ ነው የተናገሩት። በአፍሪካ ህብረት፣ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር፣ በ ዓለማቀፍ የስደተኞች ድርጅትና በሱዳን መንግስት ትብብር ባለፈው ጥቅምት ወር ሱዳን ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በሚገታበት መንገድ ዙሪያ የመከረ ዓለማቀፍ ኮንፈረንስ የተካሄደ ሲሆን፤ በኮንፈረንሱ 15 ሀገሮችና የአውሪፓ ህብረት ተወካዮች ተገኝተዋል

Sunday, March 8, 2015

ከቤተሰብ ውጪ እንዳይጠየቅ ከቶም ህክምና እንዳያገኝ….. ይህ ተመስገን የሚባል ልጅ!!
ስለ ተመስገን ለዝዋይ እስር ቤት አዛዦች የተሰጠ ትእዛዝ
ለቤተሰብ ብቻ መታየት እንዲችል ከተፈቀደ ዛሬ 18 ቀናት የሆነውን ተሜን ለማየት ዝዋይ እስር ቤት በጠዋት ደርሼ የእስረኛና የጠያቂ መገናኛ ቦታ ላይ ተቀምጬያለሁ፡፡ ተሜ ሲመጣ አየሁት እንደለማዱ በወታደሮች ተከቦ ነው የመጣሁ፡፡ አዲሱ ነገር ተሜ አረማመዱ ቀስ እያለ አንዳንዴም እየቆመ ነው የሚመጣሁ፡፡ ወታደሮቹም ሲቆም እየቆሙ ቀስ ሲል ቀስ እያሉ ነው የሚሄዱት፡፡ አጠገቤ እስኪደርስ ሁኔታውን በዝምታ እየታዘብኩ ጠበቅኩት፡፡ እየሳቀ ሰላም አለኝ፡፡ እኔ ግን ሰላምታውን በመመለስ ፋንታ “እስካሁን ህክምና አላገኝህም?” አልኩት ቀስ ብሎ እንጨቱን ተደግፎ ሲቀመጥ የህመሙን መጠን አስተዋ...
See More
Like ·  · 
የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ
ችሎት ደፍረዋል በሚል ማክሰኞ ሊቀጡ ነው
---------
የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲ አመራሮች የነበሩት የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺና አብርሃ ደስታ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ጉዳያቸው እየታየ በሚገኘው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ‹‹ችሎት ደፍራችኋል›› በሚል ቅጣት ሊጣልባቸው ነው፡፡ ወርቅ አገኛው
በሳለፍነው አርብ የካቲት 27 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው ችሎት ሐሙስ የካቲት 26 ቀን 2007 ዓ.ም በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ የሺዋስ፣ ዳንኤልና አብርሃ ‹‹በፍርድ ቤቱ ላይ አላግጣችኋል፣ የችሎቱን ሥራ ረብሻችኋል፣ ...ወዘተ›› በሚል በችሎት መድፈር ወንጀል ክስ በማሰማት የችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛ አርብ ዕለት ጥፋተኛ ብለዋቸዋል፡፡ 
የሺዋስም በፍርድ ቤት ላይ እምነት እንደሌለው በመግለጽ አስተያየቱን ሊነገር ቢጥርም ፍርድ ቤቱ ከቅጣት አስተያየት ውጪ እንዳይናገር በተደጋጋሚ ከልክሎታል፡፡ ዳንኤል ሺበሺ እና አብርሃ ደስታም በተመሳሳይ መልኩ የቅጣት አስተያየት እንዲሰጡ ተጠይቀው ስለተፈጠረው ነገር እና ችሎቱ ችግራቸውን እንዳልሰማቸው በመጥቀስ የቅሬታ አስተያየታቸውን በየተራ ለመናገር ጥረት ቢያደርጉም ፍርድ ቤቱ ከቅጣት አስተያየት ውጪ ምንም እንዳይናገሩ ንግግራቸውን በተደጋጋሚ ሲያቋርጥ ተመልክቻለሁ፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፣ አብርሃ በተናደደ ስሜት ውስጥ ሆኖ፣ ለችሎት አስተያየቱን ለመስጠት ጥረት ሲያደርግ በችሎቱ የነበሩ መሳሪያ የታጠቁ ፖሊሶች መሳሪያቸውን ጠበቅ አድርገው በመያዝ ወደእስረኞቹ ሲጠጉ እና አብርሃን የሺዋስ ወዳለበት ቦታ እንዲቀይር ሲያስገድዱት ታዝቤያለሁ፡፡
ፍርድ ቤቱም በዚሁ ዕለት የተጠቀሱት ተከሳሾች ‹‹ችሎት እያወኩ ነው›› በሚል በድጋሚ በመናገር ከነገወዲያ የካቲት 30 ቀን 2007 ዓ.ም ቅጣት ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ሀብታሙ አያሌውም ‹‹መደበኛው ችሎት መቼ ይቀጥላል?›› በማለት ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የሰባተኛ ተከሳሽ ክስ ተስተካክሎ ማክሰኞ እንደሚቀርብና ከቅጣት ውሳኔው በኋላ እንደሚቀጥል የዕለቱ ሰብሳቢ ዳኛ ተናግረዋል፡፡ እነየሺስ፣ ዳንኤል፣ አብርሃና ሀብታሙ ደስ በማይል ስሜት እንደተናደዱ እጃቸው በአንድ ካቴና ለሁለት እየታሰሩ ከችሎት ወጥተዋል፡፡
በዚህ ዕለትና ችሎት ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ እና ጦማሪ አቤል ዋበላ ነበሩ፡፡ ከርቀት ለምን እንደመጡ ስጠይቃቸው ‹‹ለምስክርነት›› አሉኝ፡፡ እስከግማሽ ቀን ድረስ ሌለ ምስክርነት እየተሰማ ስለነበረ የእነተስፋለምን ምስክርነት ማድመጥ አልቻልንም፡፡ ለከሰዓት በኃላ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡
ኢሕአዴግኣዊ ዴሞክራሲ እና ሊብራሊዝም – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ
አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅፅ 15 ቁጥር 789፣ የካቲት 28 ቀን 2007 ዓ.ም) መግቢያ ኢሕአዴግ፣ የዐፄውን ሥርዐት ርዝራዥና የደርግን አስከፊ ሥርዐት አፈራርሼ አገሪቱን በተሻለ የዴሞክራሲ ጎዳና እየመራኹ ነው በማለት ያለመታከት እያበሠረና እየወተወተ ይገኛል። ካለፈው ሥርዐት አላቅቄኣችኋለኹ የሚለው የራሱ እውነታ ቢኖረውም፣ በአንጻሩ ግን ኢሕአዴግ ራሱ የሚያበጅልን ዐዲስ ቀንበር መልክ አውጥቶ ዐደባባይ ወጥቶ...
http://netsanetlegna.wordpress.com/…/%e1%8a%a2%e1%88%95%e1%…
አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅፅ 15 ቁጥር 789፣ የካቲት 28 ቀን 2007 ዓ.ም) መግቢያ ኢሕአዴግ፣ የዐፄውን ሥርዐት ርዝራዥና የደርግን አስከፊ ሥርዐት አፈራርሼ አገሪቱን በተሻለ የዴሞክራሲ ጎዳና እየመራኹ ነው በማለት ያለመታከት እያበሠረና እየወተወተ ይገኛል። ካለፈው ሥርዐት አላቅቄኣችኋለኹ የሚለው የራሱ እውነታ ...
NETSANETLEGNA.WORDPRESS.COM

Friday, March 6, 2015

በአፋር ወጣቶች ለስለላ እየታፈሱ ነው

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፋር ነጻ አውጭ ድርጅቶች በአካባቢው እያደረሱት ያለው ተጽአኖ ያሰጋው መከላከያ፣ በአፋር የተለያዩ የጠረፍ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶችን በማፈስ ላይ ነው። ስማቸው ለደህንነት ሲባል እንዳይጠቀስ የጠየቁት ወላጆች በደርግ ጊዜ የቀረው አፈሳ በክልሉ እንደ አዲስ መጀመሩን ተናግረዋል። በርካታ ወጣቶች አፈና በመፍራት ጫካ መግባታቸውንም ነዋሪዎች አክለዋል። አርዱፍ፣ አፋር ጋድሌና የአፍዴራ ወጣቶች በቅርቡ ግንባር መፍጠራቸውን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።
በጉዳዩ ዙሪያ የክልሉን የጸጥታ ዘርፍ ክፍል ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

በደልጊ ከተማ ከቤተክርስቲያን ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰ

የካቲት ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ጣቁሳ ወረዳ ደልጊ ከተማ ለቤተክርስቲያን ማሰሪያ የተከለለውን ቦታ 40 የሚሆኑ የምክር ቤት አባላትና ደጋፊዎቻቸው መከፋፈላቸው የፈጠረው ህዝባዊ ቁጣ፣ የካቲት 27 ጧት ላይ ወደ ተቃውሞ ተቀይሮ የከተማው ፖሊስ ጣቢያ ፣ መዘጋጃ ቤት፣ መስተዳድሩና የብአዴን ጽህፈት ቤት መስኮቶችና በሮች ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው፣ ሁለት ፖሊሶችና አንድ የመዘጋጃ ቤት ዘበኛም ተደብድበዋል።
በብዙ ሺ የሚቆጠር ህዝብ የተሳተፈበትን ተቃውሞ ለማብረድ ፖሊሶች ጥይት ከመተኮሳቸውም በተጨማሪ ሰለፈኞችን በዱላ ደብድበዋል።
ለተቃውሞው መነሻ የሆነው፣ ህዝቡን ወክለው ሲከራከሩ የነበሩት አቶ ተችሎ ካሴና አቶ ፈንታ መኳንንት ተይዘው መታሰራቸው ሲሆን፣ ህዝቡ መሪዎቻችንን ፍቱልን በማለት ወደ ፖሊስ ጣቢያ አምርቷል። ፖሊስ ለህዝቡ ጥያቄ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ህዝቡ
በጣቢያው ላይ ድንጋይ መወርወር መጀመሩን የአይን እማኞች ገልጸዋል
የህዝቡ ተቃውሞ እያየለ መምጣት ያሰጋው ፖሊስ፣ ሁለቱን የህዝብ ወኪሎች ከእስር ቤት በመልቀቅ፣ ችግሩን ለማብረድ ችሎአል። ህዝቡም ወኪሎቹን ተሸክሞ በከተማው በአሸናፊት ስሜት ሲጨፍር ማምሸቱን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል

የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ

የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙ 6 የኦሮሞ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በድሎናል ሲሉ አማረሩ ። የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ግን ያልተፈታ ችግር እንደሌለና በተለይ በአባላት ላይ ይደርሳል ስለተባለው እንግልት ቦርዱ እንዳልሰማ ተናግረዋል ።
Büro des National Electoral Board of Ethiopia NEBE
ፓርቲዎቹ ከዚህ ቀደም ከተደረሰበት ስምምነት ውጭ አባላቶቻቸው እንደሚንገላቱ የበጀት ድጎማ እንደማይሰጣቸውና ለምርጫ ቅስቀሳ አመቺ የአየር ጊዜ እንደተነፈጉ ተናግረዋል ። ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ግን ያልተፈታ ችግር እንደሌለ ተናግረዋል። በጀትን በተመለከተ ለተወዳዳሪ ፓርቲዎች በሙሉ በእኩል የሚካፈፈለው ገንዘብ ሰሞኑን እንደሚለቀቅ አስታውቀዋል ።ሁለቱንም ወገኖች ያነጋገረው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

ማስተርስ/ዶክተሬት እንደ መለዋወጫ እቃ! (ታሪኩ አባዳማ)

ታሪኩ አባዳማ | የካቲት 2007
ልጄ አስራ ሁለተኛ ክፍል ስለጨረሰ የደስታዬ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ… የሚል ግብዣ ደርሷችሁ አያውቅም? እናንተም ፋሽኮ ቪኖ ወይንም እናትና ልጅ አረቄ ይዛችሁ ድግሱን ለማድመቅ ሳትሄዱ አልቀራችሁም – የዚያን ዕለት ጎረምሶቹ የቀለጠ ፓርቲ ደግሰው እስኪነጋ ይጨፍራሉ አሉ… ይህስ ይሁን።Fake Degrees Are Just A Few Clicks Away  Read more: http://www.care2.com/causes/fake-degrees-are-just-a-few-clicks-away.html#ixzz3TWjawZMT
ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ላይ መሆኑን አንድም ቀን ሲናገር ሰምታችሁ የማታውቁት በቅርብ የምታውቁት ሰው ፣ እንዲያውም በመደበኛ ትምህርት ከስንተኛ ክፍል ነበር? አቋርጦ ወደ ሄደበት ሄዶ (ጫካ ወይንም ምርኮ) ግን የዛሬ ‘ሹም’ ‘የማስተርስ ፣ ዶክትሬት ዲግሬዬ በፖሰታ ስለደረሰኝ የደስታዬ ተካፋይ እንድትሆን ብሎ ቢጠራችሁስ? ይኼ ሰው ድሮ ትምህርት ቤት የተመዘገበበት ስም ሌላ ነበር… አሁን ደግሞ አዲስ ስም ብቻ ሳይሆን አዲስ ማዕረግ ፣ አዲስ ቤት ፣ አዲስ መኪና… ምኑ ቅጡ… ባናቱ ላይ ዲግሪ ሸምቶበታል።
ይድረስ ለተከበሩ… አስፈላጊውን ክፍያ ስላጠናቀቁ የ ማስተርስ ዲግሪዎን አያይዘን ልከናል – ለዶክተሬት ዲግሪዎ ተመልሰው እንደሚመጡ ተስፋ እናደርጋለን – የዋጋ ቅናሽም እናደርግሎታለን – ስለ ደንበኝነታችን ሲሉ አገልግሎታችንን ለስራ ባልደረቦችዎ እንዲያስተዋውቁልን ትብብሮን እንጠይቃለን – ለዚህም ተገቢውን ወሮታ እንከፍላለን – ያስታውሱ ‘ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ’ – ሴንቸሪ ዩንቨርሲቲ
ታዲያ እርሶም ለምርቃቱ ተጋብዘዋል – በተጠራው ድግስ ላይ ‘…ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትህን የት ነበር የጨረስከው ፣ ማትሪክ ውጤትህስ ስንት ነበር ፣ የመጀመሪያው ዲግሪህስ… ያጠናኸው ፣ የተመራመርከው እና መቸ ያዘጋጀኸው መመሪቂያ ቴሲስ ነው ለዚህ ያበቃህ?…’ ብላችሁ ትጠይቃላችሁ ወይስ ድግሱን ተቋድሳችሁ …እንኳን ለዚህ አበቃህ ብላችሁ መርቃችሁ ትመለሳላችሁ?
አነሳስቶ ላስጀመረን ፣ አስጀምሮ ላስጨረሰን ተብሎ ባደባባይ በግልፅ ሳይተያዩ ማስትሬት እና ፒኤችዲ እንደ መለዋወጫ እቃ ‘…ኦን ላይን ኦርደር…’ ማድረግ የወቅቱ የወያኔ ሹማምንት ልዩ መታወቂያ መሆኑን ስናይ ‘ኦ ዲግሪ ሆይ ከስምሽ ጀርባ ስንት ደደብ መሸገ’ እንድንል ያስገድደናል። ባንድ ጀምበር ሚሊየነር ፣ ባንድ ጀምበር ጄነራል እናም ባንድ ጀምበር ዶክተር እገሌ መባል ወያኔአዊ ተፈጥሮ ያመጣብን በሽታ ነው። እነኝህ ሰዎች በየመስኩ በሚፈጥሩት ስፍር ቁጥር የሌለው የተዛባና ህገ ወጥ አሰራር ጉዳቱ ውሎ አድሮ አገሪቱ ላይ በሁለንተናዊ መልኩ እየተንፀባረቀ መሆኑን ለመናገር የሚያስቸግር አይመሰለኝም። አዲሱ ሚሊየነር በሙስና እና ነጠቃ ላይ የተገነባ መሆኑ ፣ ጄነራሉ ችግር ሁሉ የሚፈታው በጠመንጃ ብቻ ነው ሲል የቁጩ ማስተርስ እና ዶክተርም የነሲብ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መፍትሔ ሲያረቅ ሲያማክር… እንዲያው ተያይዞ ገደል መግባት መሆኑ ቁልጭ ብሎ አይታያችሁም?
‘…ለኢህአዴግ ታማኝ እስከሆነ ድረስ ማይም እንኳ ሚኒስትር መሆን ይችላል…’ ያለው ማን ነበር? ሙት ወቃሽ እንዳልሆን ብዬ እንጂ ይኼ ድኩም ራዕይ የተሰነቀው ገና ከጠዋቱ እንደነበር አትዘንጉ ለማለት ነው። የአሳ ግማቱ ከወደ አናቱ!!
አንኳንስ ዶክተሬት ስምንተኛ ክፍል ሲጨርሱ ካባ ለብሶ ፎቶ መነሳት ፣ የምርቃት ቀን ደግሞ ሽክ ባለ ልብስ ፣ ባጌጠ አደራሽ ፣ ሞቅ ደመቅ ባለ ስነስርዓት ዘመኑን መቋጨት እዚህ በምእራቡ አለም ጭምር የተለመደ ነው። ከዩንቨርሲቲ ሲመረቁ ደግሞ ስርዓቱ ለየት ይላል – ይኼ ሁሉ የሚደረገው ግን አንድም ትምህርት በአግባቡ የተሰጠ ለመሆኑ ይፋዊ ማረጋገጫ ለመስጠት ሲሆን – ሽፍንፍን ፣ ድብቅብቅ ተመርቂያለሁ ማለት ባካዳሚው አለም ሆነ በህብረተሰቡ ውስጥ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ መሆኑን ለማሳየት ጭምር ነው። ይህን ስል በወያኔ ተቋማት አደባባይ የተመረቀ ሁሉ ብቃቱ ተረጋግጧል ማለቴ አይደለም።
ወያኔ ሁሉንም ዘዴ እንደ አስፈላጊነቱ ይጠቀምበታል። ከገበያ መሸመት ያለባቸው ሹሞች በጀት ተይዞላቸዋል – በተጠረቡ ቤቶች ውለው አድረው ‘የሚመረቁ’ ደግሞ አሉ… ከሲቪል ኢንሲቲትዩት… ከዚህ ሰፈር ከዚያ ሰፈር ኮሌጅ… ከዚህ ከዚያ ህዝቦች ዩንቨርሲቲ… ኮብል ስቶን ጠራቢ ምሩቃን ከታማኝ የወያኔ ካድሬ ምሩቃን ጋር ተማክረው ስለጉዳዩ የበለጠ ሊነግሩን ይችላሉ።
በምዕራቡ የትምህርት አለም ግን ልጆቻችሁን አስተምረን እዚህ አድርሰናል ፣ አዘጋጅተናል ፤ ኑ ተረከቡን የሚል ጥሪ ለወላጆች ሲቀርብ – ወጣቶቹ ለመጪው የከፍተኛ ትምህርት ዘመን ወይንም ለላቀ ሀላፊነት መዘጋጀታቸውን ለማብሰር ብቻ ሳይሆን ጠንክረው በጥሩ ውጤት ያጠናቀቁትን በአርአያነት በአደባባይ በመሸለም ሌሎችም እንዲተጉ ለማበረታታት ጭምር ነው። ይህም የሚደረገው አለምክንያት አይደለም።

Thursday, March 5, 2015

ሶስት ሚሊየን ብር የሚጠጋ ወጭ የወጣበት ድልድይ የጥራት ችግር አለበት ተባለ

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአባይ  ወንዝ ላይ የተሰራዉ 108 ሜትር ርዝመት እና አንድ ነጥብ ስድስት  ሜትር ስፋት ያለው ተንጠልጣይ ድልድይ  በሃገሪቱ ብቸኛዉ የተንጠልጣይ  ድልድይ በመስራት በሚታወቀው  ሄልቬታስ ሲዊዝ ኢንተርኮኦፕሬሽን በተሰኘ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ባለፈው ታህሳስ ወር መጨረሻ በይፋ ተመርቆ ስራ ቢጀምርም፣ በምረቃው ስነስርዓት የተገኙ ባለሙያዎች ድልድዩ የጥራት ችግር እንዳለበት መናገራቸው ነዋሪዎችንና በቦታው ተገኙ አመራሮችን አስደንግጧል፡፡
በአማራ ክልል ገጠር መንገድ ስራዎች ድርጅት የቁጥጥርና ክትትል ኬዝ ቲም ባለሙያ የሆኑት አቶ ይገርማል ታምር በዝርዝር ያቀረቡት  የጥራት ችግር በምረቃ ስነስርዓቱ ለታደሙ የክልል እና የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ኃለፊዎች፣ ግንባታውን በኃላፊነት የሰራው ባለሙያ እና የአካባቢውን ነዋሪዎችን ያስደነገጠ እንደነበር በምረቃው ስነስርዓት  የተገኙ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡
40 በመቶ በሄልቬታስ ፤60 በመቶዉ ደግሞ ከዓለም ባንክ የግብርና እድገት ፕሮግራም በተገኘ ገንዘብ ወጭዉ የተሸፈነው ይህ ድልድይ ለሃምሳ አመታት እንዲያገለግል ታስቦ የተሰራ ቢሆንም  የተሰራበት የድንጋይ አይነት፣የውሃ አጠጣጡ እና ገመዶችን ወጥሮ የያዘው የግንባታ አካል ስጋት ያለበት መሆኑን ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
የዳስራ ማርያም እና የጭስ አባይ እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ዞን ደግሞ የደራ ወረዳ የተወሰኑ የገጠር ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደሮችን የዘመናት ጥያቄን የፈታ ሁኗል የተባለለት ታንኳ በር ተንጠልጣይ ድልድይ  እንዲሰራ ላለፉት ሁለት ዓመታት አርሶ አደሮች በተደጋጋሚ ለሚመለከተዉ አካል ጥያቄ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡
ሄልቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮርፕሬሽን የተባለው የግብረ ሰናይ ድርጅት በክልሉ በተለያዩ ቦታዎች የሚሰራቸውን ተንጠልጣይ ድልድዮች ስራ በብቸኝነትና  ማንም ተቆጣጣሪ በሌለበት ሁኔታ እንደሚሰራና ማኔጅመንቱም በአንድ አካባቢ ሰዎች ብቻ የተያዘ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።  ድርጅቱ በአምስት ክልሎች ከስልሳ በላይ ተንጠልጣይ ድልድዮችን እንደሰራ በእለቱ የምረቃ ስነስረአት ላይ ተገልጿል፡፡