Thursday, March 12, 2015

እንግሊዝ ከሰብአዊ መብቶች ጋር በተያያዘ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ማቋረጡዋን አስታወቀች

መጋቢት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብሉምበርግ የእንግሊዝ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደዘገበው እንግሊዝ በኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለመደጎም ትሰጥ የነበረውን እርዳታ ያቋረጠችው፣ መንግስት መጪውን ምርጫ ተከትሎ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ፓርቲ አባሎችን ማሰሩንና መዋካቡን በመቀጠሉ ነው።
የእንግሊዝ አለማቀፍ የልማት ተራድኦ ጸሃፊ ጀስቲን ግሪኒንግ ፣ እንግሊዝ አጠቃላይ የሆነ የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማድረግ መወሰኑዋን ተከትሎ፣ ቀድም ብሎ ይሰጥ የነበረው የማህበራዊ አግልግሎት ድጋፍ እንደተቋረጠ ለእንግሊዝ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርበው አስረድተዋል።
ባለስልጣኑ በኢትዮጵያ የሚፈጸመው የሰብአዊ ና የፖለቲካ ነጻነቶች ገፈፋ አሳሳቢ መሆኑ እርዳታው እንዲቋረጥ አድርጎታል። በተለይም ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ ነጻ ምርጫ የማካሄድና የጸጥታ ሃይሎችን ተጠያቂ የማድረጉ ነገር አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ለተወሰደው እርምጃ ምክንያት መሆኑን ባለስልጣኑ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።
የእንግሊዝ ተራድኦ ድርጅት በዚህ አመት 368 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም በኢትዮጵያ ብር 11 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለመስጠት አቅዳ ነበር፧ ባለፉት አምስት አመታት ከ700 ሚሊዮን ፓውንድ ያላነሰ ገንዘብ ደግፋለች

No comments:

Post a Comment