የኦሞ ስኳር ፕሮጀክቶች ግጭቶችን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ አለማቀፉ ቡድን አስጠነቀቀ
የተለያዩ የአለም አገራትን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን፣ የአፍሪካ ልማት ባንክንና ለጋሽ ተቋማትን ጨምሮ27 አባላትን የያዘውዲቨሎፕመንት አሲስታንስ ግሩፕ የተባለ አለማቀፍ ቡድን፤ በደቡብ ኦሞ በመከናወን ላይየሚገኙ ሰፋፊ የመንግስት የስኳር ፕሮጀክቶች በአካባቢውግጭቶችን ሊቀሰቅሱ እንደሚችሉ ባለፈው ረቡዕማስጠንቀቁን ብሉምበርግ ዘገበ፡፡
የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም በበኩላቸው፤ በደቡብ ኦሞ የሚከናወኑ የልማትስራዎች ግጭትን ለመከላከል ያለሙእንደሆኑና በአካባቢው የሚኖሩ ማህበረሰቦችም የልማት ዕቅዶቹንበተመለከተ በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል በስፋት መሰራቱን ከብሉምበርግጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅተናግረዋል፡፡
የስኳር ኮርፖሬሽን ከቻይና ልማት ባንክ ባገኘው ብድር በደቡብ ኦሞ አካባቢ ስድስት የስኳር ፋብሪካዎችንለመገንባትና በ150 ሺህ ሄክታር ላይየሸንኮራ አገዳ ልማት ለማከናወን እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ የጠቆመውዘገባው፣ የሸንኮራ አገዳ ልማቱ የአካባቢውን ነባር ነዋሪዎች አኗኗርሊያቃውስ ይችላል ተብሎ እንደሚሰጋ ቡድኑማስታወቁን ገልጧል፡፡
No comments:
Post a Comment