Thursday, March 5, 2015

ኦህዴድ ለ25ኛ አመት በአሉ ገንዘብ እንድናወጣ እያስገደደን ነው ሲሉ ባለሃብቶች ገለጹ

የካቲት ፳፮(ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀድሞ የሸእቢያ ምርኮኞች የተመሰረተው ኦህዴድ 25ኛ አመት የእዮቤልዩ በአሉን ድል ባለ ድግስ ለማክበር በማሰቡ በክልሉ የሚገኙ ባለሃብቶችን ስብሰባ የጠራ ሲሆን፣ የድርጅቱ ካድሬዎች ህዝቡ ገንዘብ እንዲያዋጣ በመቀስቀስ ላይ ናቸው።
የክልሉ ፕሬዚዳንት የካቲት 29 ቀን 2007  ዓም ባለሃብቶች በአሉን ስፖንሰር እንዲያደርጉ ለመጠየቅ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ስብሰባ ጠርተዋል።
ድርጅቱ ” ድርጅታችን ኦህዴድ/ኢህአዴግ 25ኛ ኣመት የብር ኢዮበልዩ የምስርታ ቧአሉን በማድመቅ ሁኔታ ለመክበርና የፋይናንስ አቅሙን ለማጠናከር ያስችለው ዘንድ አባላቱን፣ የአላማውን ደጋፊና የልማት አጋር ከሆኑት ድጋፍ መጠየቅ አስፍልጓል፣ በመሆኑም እርስዎ፣ ድርጅትዎ ድጋፍ ያድርጉልን” የሚል ደብዳቤ ለክልሉ ነዋሪዎች በትኗል።

No comments:

Post a Comment