ዶክተር ኢንጂንየር ነኝ ሲለን የነበረው አቶ ሳሙኤል ዘሚካኤል ፕሮፌሰር ነኝ ብሎ ተቀጥሮ የመንግስት ደመወዝ አልተቀበለም። ነገር ግን ስንት ስራ መስራት ያለበት መንግስት ፖሊሶች ኬንያ ድረስ አስልኮ በብዙ ወጪ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ካደረገው በኋላ በልዩ ቅልጥፍና ለፍርድ አቅርቦታል።
በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ ውስጥ ከመወለዳቸው በስተቀር ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ ምንም አይነት ትምህርት ያላጠናቀቁ ዶክተር (ፕሮፌሰር) ኮንስታንቲኖስ በርሄ የሚታወቁት ከህዋሃት ጋር የተሳሰሩና ብዙ ባለስልጣን ጓደኞች እንዳላቸው ነው። በመገናኛና በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ለህዝብ፣ ለመንግስትም ሆነ ለራሳቸው ጓደኞችና ቤተሰብ ሳይቀር መዋሸታቸው ታውቆ አሁንም ፕሮፈሰር እየተባሉ ለማንም ሌላ ፕሮፌሰር የማይከፈል 18445 ብር ደመወዝ በወየወሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይከፈላቸዋል።
ሬዲዮ ፋና አቶ ሳሙኤል ዘሚካኤል ለማዋረድ የተጠቀመበትን ጊዜ ግማሽ ያህል አቶ ኮንስታንቲኖስ በርሄ ላይ ቢጠቀም ጥሩ ነበር። እኛ ጎሰኞች አይደለንም። በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ስለሆነ ህዋሃትን አፍቃሪ ትግሬም ቢሆኑም አቶ ኮንስታንቲኖስ በርሄ እንደ አቶ ሳሙኤል ዘሚካኤል ለፍርድ ይቅረቡ...
አቶ ኮንስታንቲኖስ በርሄ እንደ ታዋቂ ምሁር የክብር እንግዳ ሆነው እንደ ፕሮፈሰር በየስብሰባው ከፊት ወንበር እየተያዘላቸው ይጋበዙ ነበር። ሰሞኑን ግን የት እንደገቡ አልታወቀም።
No comments:
Post a Comment