Monday, April 27, 2015

በስደት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙትን አሰቃቂ ድርጊቶች የሚያወግዙ ሰልፎችንና የሻማ ማብራት ስነስርአቶች ተካሄዱ

ሚያዝያ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባሳለፍነው ሳምንት በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ግፍ የሚቃወሙ ሰልፎች፣ የሻማ ማብራት ስነስርአቶችና ጸሎቶች በአውሮፓ፣ በአሜሪካና በእስያና
በአውስትራሊያ ተካሂዷል። በለንደን ሰኞ ሚያዚያ 19 ቀን 2007 ዓም በተካሄደው ከፍተኛ ተቃውሞ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ የደረሱትን በደሎች አጥብቀው ኮንነዋል። ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ በስፍራው ተገኝቶ እንዳለው እስከ አንድ ሺ የሚጠጉ
ኢትዮጵያውያን ከትራፋልጋር ስኩየር በመነሳት ወደ እንግሊዝ ፓርላማ አምርተዋል። በኒዉዚላንድ ኦክላንድ  የኢትዮጵያ ትንሳኤ መወያያ መድረክ ባዘጋጀዉ የሻማ ሥነስርዓት ላይ ኢትዮጵያኑ የሻማ ማብራት ሥርዓት  አካሒደዋል፡ ፡
በጃፓን ቶክዮ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።
በስዊዘርላንድ ጄኔቫ፣ በዙሪክ፣ በርን፣ ሴንት ጋለን፣ ባዝል፣በፈረንሳይ ፓሪስ፣ በሆላንድ አምስተርዳም፣ በአውስትራሊያ ፐርዝ ፣ በጀርመን ፍራንክፈርት ፣ በሉክሰንበርግ ፣በኖርዌይ አስሎ፡በግሪክየህሊና ጸሎት ተካሂዷል።
በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በግብጽ እና በካይሮ በኩል ለማውጣት እንቅስቃሴ መጀመሩን ቢያስታውቅም፣ ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያን ትሪፖሊ ለሚገኘው የመንግስት ተወካይ ስልክ ደውለው ምላሽ
ማጣታቸውን ተናግረዋል። ግብጽ የሚገኘው ኢምባሲ የሚሰጠው የስልክ ቁጥር አይሰራም በማለት አቤቱታ እያቀረቡ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ በቁጥጥር ስር ውለው ከነበሩት ከ1 ሺ በላይ ወጣቶች፣ አብዛኞቹ ተፈትው ከ150 ያላነሱት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ ተቃውሞውን ያስነሱት ሰማያዊ ፓርቲና አንድነት ፓርቲዎች ናቸው ብሎአል። ሰማያዊ ፓርቲ የመንግስትን ክስ  ወዲያው ውድቅ ሲያደርገው፣ አዲሱ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ትዕግስቱ አወሉ አንዳንድ አባሎቻችን ከእኛ እውቅና ውጪ ሰልፍ ላይ
ተገኝተዋል ብለዋል።  አቶ ትእግስቱ 1 የብሔራዊ ም/ቤት አባላችንና ሌላ 1 ጸሃፊ ሰልፉ ላይ መገኘታቸውን ከፖሊስ የምርመራ ሪፖርት ላይ ተመልክቻለሁ ብለዋል። የአቶ ትእግስቱ ንግግር በኤፍ ሬዲዮኖች እንዲራገብ የተደረገ ሲሆን፣ ንግግሩ ብዙ የአዲስ አበባ
ነዋሪዎችን ማበሳጨቱ ታውቋል።
አዲሱ የአንድነት ፓርቲ የኢህአዴግ ተለጣፊ መሆኑን ከዚህ በላይ ማሳያ የለም በማለት የህዝብ አስተያየት በማሳባሰብ ዘጋቢያችን በላከው መረጃ ላይ ጠቅሷል።

Friday, April 10, 2015

The ruling Ethiopian People Revolutionary Democratic Front (EPRDF), which came to power in 1991 after a guerilla war against the bloody Mengistu Haille Mariam regime, holds total political sway. The coalition, which consists of four political parties, holds 499 out of the 547 national assembly seats.
To illustrate the country’s political intolerance, the government often refers to the opposition in derogatory terms like “chauvinists”, “narrow nationalists”, “secessionists” or simply “enemies”.
The Ethiopian government controls all spheres of life, from media to people’s daily lives. The main national broadcaster, Ethiopian Television, and most of the 10 radio stations, are owned by the government. Introduced in 1992 and giving the police sweeping powers to detain journalists without trial and shut down dissenting media outlets, Ethiopian media laws make the National Security (Amendment) Bill 2014 look like a legal walk in the park.
The ruling Ethiopian People Revolutionary Democratic Front (EPRDF), which came to power in 1991 after a guerilla war against the bloody Mengistu Haille Mariam regime, holds total political sway. The coalition, which consists of four...
ECADFORUM.COM
Like · Comment · 

Thursday, April 9, 2015

በዞን 9 ጸሃፊዎች ላይ ማስረጃ ሊቀርብ አልቻለም ተባለ

መጋቢት ፩(ሚያዝያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ ዞን 9 በመባል በሚጠሩት ወጣት ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ላይ የመንግስት አቃቢ ህግ ጠንካራ ማስረጃ ለማቅረብ አለመቻሉን ጠበቃውን አቶ አምሃ መኮንንን በመጥቀስ ዘግቧል።
በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት 6 የዞን ዘጠኝ እና 3  ጋዜጠኞች ላለፉት 10 ወራት በእስር ላይ ከቆዩ በሁዋላ፣ ፍርድ ቤቱ በቅርቡ ምስክሮችን የመስማት ሂደቱን ጀምሯል።  ይሁን እንጅ እስካሁን ባለው ሂደት የቀረቡት ምስክሮች ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ተይዘው ቤታቸውና መስሪያ ቤታቸው ሲፈተሽ በታዛቢነት የነበሩ እንጅ ፣ ተከሳሾቹ በተለይም ክስ ከቀረበባቸው ከግንቦት7 እና ከኦነግ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው የሚያመላክት ምስክር ሊቀርብባቸው አልቻለም።
አቃቢ ህግ 35  የሰው ምስክሮች አሉኝ ብሎ ለፍርድ ቤቱ ቢያስታውቅም ” ምስክሮችን አላገኘሁዋቸውም” በሚል ሰበብ እስካሁን ሊያቀርባቸው አልቻለም። አቃቢ ህግ ወንጀሉን ያስረዱልኛል የሚላቸውን የሰው ምስክሮች በመጪው ወር መጨረሻ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤት ትእዛዝ አስተላልፏል።
በኢትዮጵያ ባለው የተበለሸ  የፍትህ ስርአት ዜጎች ዋስትና አጥተው በእስር እየተሰቃዩ ነው በማለት አለማቀፍ ድርጅቶች በተደጋጋሚ ክስ ያሰማሉ። እውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ በርካታ ጋዜጠኞች፣ ፖለቲካኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በሽብር ወንጀል ተወንጅለው በእስር ቤት ይሰቃያሉ። መንግስት ከአለማቀፉ ማህበረሰብ እስረኞችን እንዲፈታ ተደጋጋሚ ጥሪ ቢቀርብለትም ፣ ለመፍታት ፈቃደኛ አልሆነም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በማእከላዊ እስር ቤት የሚገኙ በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ እስረኞችን ፣ መንግስት የይቅርታ ደብዳቤ እንዲፅፉ ለማግባባት እየሞከረ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። መንግስት የይቅርታ ደብዳቤ ከጻፉ እንደሚፈታቸው ቢገልጽም፣ የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ግን ፣ በአብዛኛው ተከሳሾች ላይ በቂ ማስረጃ በመጥፋቱ መንግስት እስረኞቹ የሚጽፉትን ደብዳቤ እንደማስረጃ በመጠቀም በፍርድ ቤት ሊወነጅላቸው ያስባል። ከአዲስ አበባ እና ከተለያዩ ክልሎች የመጡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያን በማእከላዊ እስር ቤት በስቃይ ላይ ይገኛሉ።

በአዲስአበባ የኤሌክትሪክና ውሃ መቆራረጥ ተባብሶ ቀጥሎአል  

መጋቢት ፩(ሚያዝያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስአበባ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና የመጠጥ ውሃ መጥፋት ባሳለፍነው ሁለት ሳምንታት ተባብሶ መቀጠሉ ህብረተሰቡን ለተለያዩ ወጪዎችና እንግልት እየዳረገ መሆኑንና በዚህ ጉዳይ መንግስት የሚሰጠውን መግለጫ ማመን የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን ነዋሪዎች ገለጹ።
የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ነዋሪዎች በተለይ ባለፈው ሳምንት እና በያዝነው ሳምንት የኤሌክትሪክ ኃይል ለረጀም ሰዓታት እንደሚጠፋ ተናግረዋል፡፡ በአዲስአበባ የኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጡ በአንድ ጊዜ ድፍን ከተማዋን የሚሸፍን መሆኑና የሚቆበት ጊዜም ወደአንድ ሙሉ ቀን ወይንም ሌሊት መቀየሩ ደግሞ ግራ የሚያጋባ መሆኑ ታውቆአል፡፡
የመጠጥ ውሃ መቆራረጥም ከጊዜ ወደጊዜ ሊሻሻል ይችላል የሚል ተስፋ እንደነበራቸው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ገልጸው፣  ነገርግን በአሁኑ ሰኣት ውሃ የማይኖርባቸው ቀናት እየጨመሩ መምጣታቸው አሳሳቢ እንደሆነባቸው ተናግረዋል፡፡ አንድ በካዛንቺስ አካባቢ በአነስተኛ ምግብ ቤት ንግድ የሚተዳደሩ ነዋሪ ውሃ የሚጠፋባቸው ቀናት በአሁኑ ወቅት በተከታታይ ለሶስትና ለአራት ቀናት እየሆነ መምጣቱ አስደንግጦናል ካሉ በኃላ፣  ኤሌክትሪክም ቢሆን ደጋግሞ መቆራረጡ ምግብ ለማብሰል ባለመቻላቸው ለተጨማሪ ወጪና ኪሳራ እየተዳረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡  አያይዘውም ውሃ መጣ ሲባል ኤሌክትሪክ እየጠፋ፣ ችግሩም ዕለት ከዕለት እየተባባሰ ኑሮአችንን እያመሰቃቀለ ነው ብለዋል፡፡
በተለይ ከኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ በርካታ አገልግሎት ሰጪ መንግስታዊ መ/ቤቶች ስራ እየተደናቀፈ ከመሆኑም በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የኤክስፖርት ትዕዛዝ ማሟላት አለመቻልና ሠራተኞቻቸውን እስከመቀነስ አድርሶአቸዋል፡፡ “በመንግስት በኩል ችግሩን እየፈታን ነው፣ አዳዲስ የውሃ ጉድጓዶች እየቆፈርን ነው፣ያረጁ የኤሌክትሪክ መስመሮችን በአዲስ እየቀየርን ነው” ከማለትና ተስፋ ከመስጠት ያለፈ ችግር ፈቺ መፍትሔ እየሰማን አይደለንም ያሉት ነዋሪዎቹ፣ አሁን አሁን ችግሩን ለመፍታት መንግስት አቅም እንደሌለው እየተረዳን በመምጣታችን ከንግግሮቻቸው ምንም ቁምነገር መጠበቅ ትተናል ብለዋል፡፡
ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በአሁኑ ወቅት ከእነዚህ መሰረታዊ የህዝብ ችግሮች ይበልጥ የመጪው ምርጫ ጉዳይ እያሳሰበው በመሆኑ፣ ከምርጫው በፊት መፍትሔ የማግኘታቸው ነገር እንዳሳሰባቸውም ያነጋገርናቸው ወገኖች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ከከተማው ሕዝብ ከ75 በመቶ በላይ 24 ሰኣታት ውሃ ያገኛል ሲሉ መግለጫ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

Tuesday, April 7, 2015

በአለማቀፍ ድርጅቶች እርዳታ ከአንድ መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ከየመን ወደ አገራቸው ተመለሱ

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት _IOM ባወጣው ዘገባ ህይወታቸው በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 131 ኢትዮጵያውያንን ከጅቡቲ ወደ አገራቸው መልሷቸዋል።
ከተመላሾቹ መካከል 100 ያህሉ ኢትዮጵያውያ ወደ የመን ለመጓዝ በዝግጅት ላይ እንደነበሩ ድርጅቱ አስታውቋል። 28 ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከየመን ወደ ጅቡቲ በባህር ላይ ጉዞ አድርገው የደረሱ ናቸው።
በሰላም ወደ አገራቸው ከተመሰሉት መካከል አንድ እርጉዝ ሴት እና 37 ወላጅ አልባ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ድርጅቱ ገልጿል።
አይ ኦ ኤም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በየመን በሚካሄደው ጦርነት የተነሳ መውጫ አጥተው እየተሰቃዩ ነው  ብሏል። ከተለያዩ መንግስታት የቀረቡለትን ጥያቄዎች ግምት ውስጥ በማስገባት ድርጅቱ 11 ሺ የሚሆኑ የውጭ አገር ዜጎችን ከየመን ለማውጣት
እንቅስቃሴ እንደሚጀምርም አስታውቋል። አንዳንድ አገሮች በየመን ላይ ያየር ጥቃት ከምትፈጽመዋ ሳውዲ አረቢያ ፈቃድ እየጠየቁ ለተወሰኑ ሰአታት አውሮፕላን እየላኩ ዜጎቻቸውን ለማስወጣት ችለዋል።
የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያውያኑን የማስወጣቱን ሃላፊነት ለአይ ኦ ኤም ሳይሰጥ እንዳልቀረ ምረጃዎች ያመለክታሉ።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቻይና የባህር ሃይል ሰራተኞች ድጋፍ ወደ አገራቸው የገቡ 30 ሰዎችን ” የመጀመሪያው ዙር ስደተኞች ወደ አገራቸው ገብተዋል” ብለው ከሳምንት በፊት ቢያስታውቁም፣ ከዚያ በሁዋላ መስሪያ ቤታቸው ያለው ነገር የለም።

ገዢው ፓርቲ የጦርነት ያክል ዘምቶብናል ሲሉ የኦፌኮ ሊቀመንበር ተናገሩ

መጋቢት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ አባል የሆነው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊ/መንበር አቶ በቀለ  እንደተናገሩት በመጪው ምርጫ ለመሳተፍ ድርጅታቸው በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች እጩዎችን ቢያሰማራም፣ እጩዎቹ እየታሰሩና
እየተደበደቡ በመሆናቸው መድረክ ቀጣዩን ሂደት ለመወሰን እየተነጋገረ ነው።
አቶ በቀለ በሆድሩ ጉድሮ አባሎቻቸው ቅስቀሳ እንዳያደርጉ መከልከላቸውን፣ በሜታ ሮቢ  ከ50 ያላነሱ ወጣቶች መታሰራቸውን፣ በግንደበረት የወረዳው አስተዳደር ሽጉጥ በማውጣት  አባሎችን ማስፈራራታቸውን ፣ ግንጭ ላይ ጽ/ቤታቸው መሰበሩን እና ሌሎችንም
እየደረሱባችው ያሉትን ችግሮች ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድም ሆነ ፖሊስ መልስ ሊሰጡዋቸው እንዳልቻሉ የገለጹት አቶ በቀለ፣ ጥቃቱና ዘመቻው የማይታገስ ከሆነ መድረክ ስለሚወስደው እርምጃ እየተነጋገረ ነው ብለዋል።
የፊታችን ግንቦት የሚደረገው ምርጫ አለማቀፍ ትኩረት አልሳበም። የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የካርተር ማእከል ምርጫውን እንደማይታዘቡ ይታወቃል  ገዢው ፓርቲ አንጻራዊ የሆነ ፉክክር ከሰማያዊ ፓርቲ እና ከመድረክ ይገጥመዋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በድርጅቶች ላይ
የሚደረሰው ጫና ብዙዎች ነጻ ምርጫ ይካሄዳል ብለው ተስፋ እንዳይጥሉ አድርጓቸዋል።